ኢትዮጵያ የራሷን የነዳጅ ምርት መጠቀም መጀመሯ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ የራሷን የነዳጅ ምርት መጠቀም መጀመሯ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ የራሷን የነዳጅ ምርት ለአገር ውስጥ ፍጆታ መጠቀም ጀምራለች።  በዚህም መሰረት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ባለፉት 6 ወራት 1650 በርሜሌ ድፍድፍ ነዳጅ ለአገር ውስጥ ገበያ መቅረቡን ይፋ አድርጓል::

በያዝነው ሣምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሊቀርብ በተዘጋጀው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት በሙከራ ደረጃ መመረት የጀመረው ነዳጅ ባለፉት 6 ወራት ለአገር ውስጥ ገበያ ሲቀርብ መቆየቱን ያስረዳል ተብሎ ይጠበቃል::

ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ ላለፉት 6 ወራት 1650 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለአገር ውስጥ  ገበያ መቅረቡንና በዚህም አገሪቱ ከውጭ ተገዝቶ ለሚገባ ነዳጅ ታወጣ ከነበረው የውጭ ምንዛሪ 55 ሺኅ 994 ዶላር ማዳን መቻሏን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ድረ ገጽ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል::

በኦጋዴን የሚገኘውን የነዳጅ ምርት ከአገር ውስጥ ገበያ  ባሻገር ወደ ውጪ ለመላክ ከኦጋዴን እስከ ጅቡቲ የውስጥ ለውስጥ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ በቅርቡ እንደሚጀመር ከሳምንታት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

LEAVE A REPLY