ክቡር ጠቅላይ ምኒስቴር፤
ኢትዮጵያችን የክርስትና፤ ጁደይዝምና እስልምናን ቀድማ በመቀበል የእምነት ማህደር ሆና ለዘመናት ቆይታለች። ቤተእምነቶች በቀኖና ይለያዩ እንጂሁሉም ስለፍቅርና አብሮነት ሲአስተምሩ ነረዋል። ለሕዝባችን ፈሪሃ እግዚአብሔርን፤ ስብእናንና ይሉኝታን አላብሰው መንፈሰ ጠንካራ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ረድተዋል። ኢትዮጵያ የሰላም፤ የፍቅርና የአብሮነት ብቸኛ ደሴት ሆና እንድትቆይ የበኩላቸውን አበርክተዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብሮነት እየላላ፤ መቻቻል ፍክክር እየሆነ መጧል። ለዚህ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋናው ግን የ፮፮ቱ የግራ ዘመም ፖለቲካ መዘዝ እንደሆነ ይታመናል። ዓብዮት ልጆቿን ትበላለች፤ አላርፍ ያለች ነብር ዘጠኝ ትወልድና ልጆቿ ያልቃሉ እርሷም ትሞታለች ብሎ መዘመር ሲጀመር ነገር ሁሉ ተበላሸ። በደም የተዋሃደ፤ በባሕል የተቆራኘ፤ በመልክና በአኗኗር የተመሳሰለን ሕዝብ አንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ፤ አንዱን በዝባዥ ሌላውን ተበዝባዥ አርጎ በመሳል እርስ በርሱ እንዲጫረስ፤ አገርም እንድትፈርስ ስራ ተሰርቷል። የሕውሃት መንግሥትም ለስልጣኑ ሲል የዘር ፖለቲካውን ሕጋዊ ሽፋን ሰጦ ሲያስተምርና ሲአተርማስ አንድ ትውልድ እንዲመክን አርጓል።
ሕውሃት ስልጣን ይሻማኛል ያለውን የዓማራ ብሔር በጠላትነትፈርጆ በሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች እንዲጠላ ብዙ ቆሻሻ ስራሰርቷል። ዓማራን፤ አማርኛንና ኦርቶዶክስን የአንድ ሳንቲምገጽታዎች አርጎ በመሳል ለማጥፋት ሰፊ ስራ ሰርቷል። በፈሪሃ እግዚእብሔር የታነፀው ሕዝባችን ግን ተንኮሉን ሁሉ አክሽፎታል። ምስማር ሲመቱት እየጠበቀ እንደሚሄደው አማራነት፤ ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክስ እያጠነከሩና እየጨምሩ መጡ እንጂ አልደከሙም፤ ለመለሙ እንጂ አልጠፉም።
ዶክተር ዓብይ ሆይ፤ ይህን ቆሻሻና ኢሰባዊ የፖለቲካ መስተጋብር ከበከት አስተዳደር ጋር እንደተረከቡ እንረዳለን። አራሙቻውን ነቅለው ለመጣልና የተስፋይቱን ምድር ኢትዮጵያን ለማስተካከልፈተና እንደሚገጥምዎት ከጅምሩ ገብቶናል። ወደ ምንፈልጋት ኢትዮጵያ አልጋ ባልጋ ያሸጋግሩናል የሚል ቀቢጸ እምነትም አልነበረንም። እንዳሰብነውና እንደፈራነው ኢትዮጵያን ለማሻገር በጀመሩት የመደመር እሳቤ ውስብስብ ፈተና ከወዲሁ ገጥሞዎታል። ጥርስ አልባው ፍቅር ያሸንፍል መርህዎ ለዚህፈተና እንዳገለጠዎ የምናምን ብዙዎች ነን።
ለምን ቢሉ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ቆምጫጫ ውሳኔና እርምጃ መውሰድ አለመቻልዎል ፈተናዎን አብዝቶታል። በብዙዎች እይታከሆነ በፍቅር ብቻ ያሸነፈ አመራር አይታወቅም። ፍቅር የከንፈር ወዳጅን ታሸንፋለች፤ ወዳጅ ዘመድንና ማህበረሰብን ታቀራርባለች፤ የማስተዳደር በሃሪ ግን የላትም። ቀኝህ ሲመታግራህን ስጥ የሚለው የሃዲስ ኪዳን አስተምህሮት በሰዎች መካከል የሚነሱ አምባጓሮዎችን ሊአርቅ ይችል እንደሆነ እንጂሃገር አያስተዳድርም።
ሃገር ከሆድ ይሰፋል እንዲሉ በሰፊው አውድማ ውስጥ ፍቅር የማይገዛውን ሕግ ሊገዛው ይገባል። ስርዓተ መንግሥት ባልነበረበት ህብረተሰብና ባልበለፀጉ ሃገራት እንኳን ማህበራዊሕጎችን ተጠቅመው ስርዓትን አስፍነው ኖረዋል። እርስዎ የፈለቁበት ማህበረሰብ በገዳ ስርዓተ ሕግ ተስተዳድሯል። በሌሎች አካባቢዎችም የደቦና ጅጌ፤ የአፍርሳታ ሕጎች አውጥተው አስተዳድረዋል።
አገር ከዚህ ስለሚለይ በሕግ መተዳደር ይኖርበታል። ሕግ አርቃቂ፤ ሕግ አስከባሪ፤ ሕግ አስፈጻሚ የሚአስፈልገውም የሕግየበላይነትን ለማምጣት ነው። አገር የሚአስተዳድር መሪ ሕግ የማስከበር፤ የሕብረተሰብ ደህንነትን የማስጠበቅ ኅላፊነት አለበት። ይህን ማስጠበቅ ያልቻለ መሪ ሃገርን ለብጥብጥ፤ ለስርዓተ አልበኝነትና ለውድቀት ይዳርጋል።
ሕግ ባልተከበረበት ሁኔታ ዜጎች ሕግን በእጃቸው ለማስተናገድ ይገደዳሉ። የመንጋ ፖለቲካና የመንጋ ፍርድ ፍርድቤቶችንና ፖሊስንተክተው ይሰራሉ። መሪዎችና አስተዳዳሪዎች የሃገሪቱን ሕገመንግሥት ማክበር ሲሳናቸው መንጋው እራሱ ሕግ አውጭ፤ ሕግአስፋጻሚ፤ ሕግ አርቃቂ ይሆናል። ለምሳሌ አንድ የውጪ ዜጋ (ጃዋር) በሰው ሃገር ገብቶ የፖለቲካ ቅስቀሳና ትርምስ ማድረግ በመቻሉ ከኢትዮጵያ ሕግ ውጪ እራሱ ሕግ ሆኖ ይንቀሳቅሳል።የዶ፨ር መረራ ጉዲናው ኦፌኮም ከሕግ ውጪ ኢትዮጵያዊዜግነት ሰጦ የቀበሌ መታወቂያ ሸልሞታል። መረራ የመንግሥት ስልጣን ቢይዙ ምን ሊአደርጉ እንደሚችሉ መተንበይ አያዳግትም።
ክቡር ዶ/ር ዓብይ ከዚህ በላይ የስርዓት አልበኝነት ማሳያ ምንሊኖር ይችላል። ሕግ በማይከበርበት ሃገር ግለሰቦችና ድርጅቶችሕግ መሆን ሲጀምሩ ቀይ መስመር ማለፈቻው ታውቆ ሕጋዊእርምጃ አለመወሰዱ ዜጎችን እያነጋገረ መሆኑን ያጡታል የሚልእምነት የለም።
በንጉሱ ጊዜ በሕግ አምላክ ብሎ የሚገዳደርን ሕዝብ አውርዶ ሕጋዊ ደንቆሮ ማድረግ አይገባም። ለዛውም በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን፤ ሳተላይት ወደሕዋ በላክንበት ጊዜ። እንዲህ ዓይነቱን ጋጠወጥነት በፍቅር እናሸንፋለን ብሎ ዝም የሚልን ሃገርና መሪ ሳተላይታችንም ፈልጋ ልታገኘው አይቻላትም።
በቅርቡ የዓማራ ተማሪዎች ባልታወቁ ወንበዴዎች ታፍነው ደብዛቸው ጥፍቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት የሚሰጠው የተምታታ መረጃ እርስ በርሱ የሚጣረስ ሆኗል። መንግሥትን ስርዓት አልበኛ እስኪ አስመስለው ድረስ ተቃርኗል።። ግራ እጅ የሚሰራውን የቀኙ እንዲአውቅ የሚአስችል የአስተዳደር ተዋረድየሌለ አስመስሎታል። በሕግና በመመሪያ የማይመሩና ሃይ የሚልመሪ ያለ አይመስልም። ይህ ደግሞ ለርስዎ መንግሥት እራሱንየቻለ ፈተና ነው። በመንግሥት ውስጥ ስርዓት ሲጠፋ፤ በሕዝብመሃል ስርዓት አልበኝነት ሲነገስ ሃገርና ሕዝብ ይረበሻል፤ ያኔየምጽዓት መጀምሪያው ይሆናል።
በአማራው ክልል መሬት አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግያየነው የሕዝብን ጨዋነት፤ ሕግ አክባሪነትና ሰላም ፈላጊነትንነው። ሰልፈኛው ሕግን አክብሮ ምንግስትን ሕግ እንዲአስከብር በመጠየቅ ሎጆቻችንን መልሱልን ሲል ጠይቋል። አያይዞም መንግሥት ሕግ ማስከበር የማይችል ከሆነ እጅ አጣጥፈን አንቀመጥም ሲል ጩኸቱንና የማስጠንቀቂያ ድወሉን አቃጭሏል። መልእክቱም ሕግ ካላስከበራችሁ በራሳችን ሕጉን እናስከብረዋልን ነው። ይህ ሲሆን ነው ስርዓት አልበኝነት የሚነግሰው። የእርስ በርስ ፍጅትም የሚቀሰቀሰው።
ክቡር ጠቅላይ ምንስቴር፤ ፍቅር ያሸንፋል የሚለው መርህ እናአቋም ወንዝ አያሻግርም። በፍቅር ለመምራትና ለማስተዳደርከፈለጉ ለፍቅር መስተዳድር የሚአስፈልገውን የመጫወቻ ሕግበቅድሚያ ማመቻቸትና ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብዎታል።ሃገር በመጽሃፍ ቅዱስና በቁራን ቀኖና አይተዳደርም።ምክንያቱም ሕግ ወገነተኘነቱ ለሕዝብና ለሃገር ሲሆን የእምነትቀኖና ወገንተኝነቱ ለምእመኑ ብቻ ነው።
በመደመር እሳቤ ዴሞክራሲን ማምጣት ማሰብዎ ይደገፋል።ዴሞክራሲ ሲሰፍን ጦርነት፤ የእርስ በርስ ብጥብጥ ይወገዳል።እርስ በርሱ የሚከባበርና የሚፋቀር ሕዝብ ይፈጠራል።ዴሞክራሲ ሊገነባ የሚችለው ደግሞ የህግ የበላይነት ሲከበርነው። በሃይማኖት ቀኖና ተመርተው የበለጽጉ፤ ዴሞክራሲ የገነቡሃገራትን አናውቅም፡በሕግ እንጂ።
ክቡር ዶ፨ር ዓብይ፤ የሕግ የበላይነትን ቀዳሚ ተግብርዎ አድርገውየተስፋይቱን ምድር ተስፋና ብልጽግናን ያጎናጽፏት። ከዚህ ውጪያለው አማራጭ ለሃገርም፤ ለሕዝብም ጠቃሚ ስላልሆነቆምጨጭ ብለው ይምሩን። በርስዎ ተስፋ እንድንቆርጥአይገፋፉን። ኢትዮጵያን በሚሰብክ መሪ ላይ ተስፋ ከከቆረጥንበኢትዮጵያ ተስፋ ቆረጥን ማለት ነው። በሃገር ደግም ተስፋአንቆጥርምና ይበርቱ።
ሰማነህ ጀመረ
ካናዳ፤