በስድስት ወር ውስጥ ለ1,270 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል ተባለ

በስድስት ወር ውስጥ ለ1,270 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በ2012 ዓ.ም በግማሽ በጀት ዓመት ለ1,270 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ዘለቀ ደላሎ ተናገሩ፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ 2,934 ታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ቀርቦና ተመርምሮ አስፈላጊው መረጃና ማስረጃ መሟላቱን በማረጋገጥ ለቦርድ እንዲቀርብና እንዲወሰን መደረጉ ተገልጿል።

የቀረቡ የይቅርታ ጥያቄዎችን በመመርመር ውሳኔ ለማሰጠት የ2,934 የታራሚዎች ቀርቦ አስፈላጊው መረጃና ማስረጃ መሟላቱን በማረጋገጥ ለ1,270 ታራሚዎች ብቻ ይቅርታ ተደርጎላቸዋል ሲሉ ባለሥልጣኑ አስታውቀዋል፡፡

በይቅርታው ከመከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች፣ በክልል ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸዉ የፌዴራል ፍርድ ቤት ስልጣንና ሓላፊነት የሆኑ እንደ ቼክ፣ ሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውርና መሰል ጉዳዮች፣ በፌዴራል ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው በክልል የሚታረሙ፣ በዝውውር በክልል ታስረው ያሉ ታራሚዎች ተጠቃሚ መሆናቸዉ ተጠቁሟል፡፡

1,664 ታራሚዎች የፈፀሙት ወንጀል የህዝብንና የመንግስትን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በአግባቡ የታረሙ ባለመሆኑና አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ስርቆትና ውንብድን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ በይቅርታ እንዳይካተቱ በመደረጉ ምክንያት፣ የህዝብንና የመንግስትን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ቦርዱ የይቅርታ ጥያቄያቸዉን ውድቅ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

በልዩ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ ይቅርታ የተደረገላቸዉ ታራሚዎች እንዳሉ የጠቆሙት አቶ ዘለቀ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለማነጽ በማይመች ሁኔታ ዉስጥ የሚገኙ፣ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በማይድን ህመም የተያዙ 30 ታራሚዎች ፣ በእድሜ መግፋት ምክንያት 21 ታራሚዎች፣ እንዲሁም 49 የውጭ አገር ዜጎች በልዩ ሁኔታ ጉዳያቸዉ ታይቶ ይቅርታ ተደርጎላቸዋል፡፡

 በአገር ዐቀፍ ደረጃ የይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም መመሪያን ወጥና ተገማች ለማድረግ የተጀመረውን ጥናት በማጠናቀቅ ከክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደርና ሓላፊዎች ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑንንም ሓላፊው ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY