ኤርትራዊው የህክምና ተማሪ በእንግሊዝ ተገደ

ኤርትራዊው የህክምና ተማሪ በእንግሊዝ ተገደ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || እንግሊዝ ውስጥ ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቃት ተፈጽሞበት የነበረው ኤርትራዊው የህክምና ተማሪ የግድያ ወንጀል እንደተፈጸመበት ፖሊስ ይፋ አደረገ።

በጥር ወር መጨረሻ ላይ ከአንድ ካፌ ውጪ ተከስቶ በነበረ ከፍተኛ ጸብ መካከል ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል ተወስዶ የነበረው የ33 ዓመቱ አማኑኤል ገብርኤል ስምኦን፣ ማክሰኞ ዕለት ህይወቱ አልፏል። ሆስፒታል ውስጥ ህይወቱ ያለፈው ኤርትራዊው ተማሪ በእረፍት ላይ የነበረ ሲሆን፣ ትምህርቱን ሊድስ ከተማ ውስጥ ሊቀጥል እንደነበረ የማንችስተር ፖሊስ ገልጿል።

” አማኑኤል ትልቅ ህልምና ፍላጎት የነበረው ብልህ ወጣት ነበር” ሲሉ  የሟች ቤተሰቦች ምስክርነት ሰጥተዋል። አማኑኤል ለሞት ከዳረገው ጥቃት ጋር በተያያዘ ምርመራውን የያዙት መርማሪ ካርል ጆንስ፣ ስለ ድርጊቱ የሚያውቁ ሰዎች ምስክርነት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበው ክስተቱን “አሳዛኝ ድርጊት” በማለት ገልጸውታል። በተፈጸመበት ጥቃት ህይወቱ ያለፈው አማኑኤል ገብርኤል ወደ ብሪታኒያ የሄደው ከአስራ ሁለት ዓመታት በፊት እንደነበርም የእንግሊዝ ፖሊስ ይፋ አድርጓል::

LEAVE A REPLY