በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር የተገነባው የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ሥራ ጀመረ

በአንድ መቶ ሚሊዮን ብር የተገነባው የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ሥራ ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል የመጀመሪያ ምዕራፍ በይፋ ተመርቋል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሓላዎች ተገኝተዋል። በተጨማሪም በገዳሪፍ ዋና አስተዳዳሪ ሜጀር ጀነራል ነስረዲን አብዲ የተመራ ልዑክም በምረቃ ሥነ ሥርርዓቱ ላይ ተገኝቷል።

የወደቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ የ3 ሄክታር ግንባታ በጠጠር ንጣፍ የተዘጋጀ የኮንቴነርና የተሽከርካሪ ማስተናገጃ ተርሚናል፣ 500 ሜትር ካሬ መጋዘን፣ የቢሮ ህንፃ፣ የመዳረሻ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የጥበቃ ማማ እና የዙሪያ አጥር ያሟላ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የጥልቅ ውሃ ጉድጓድና የውሃ መፋሰሻ ሥርዓት እንዲሁም መጠባበቂያ ጀነሬተርን ጨምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና ሌሎችም አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል። ወደቡ 75 ቶን ዕቃ መያዝ የሚችል መጋዝን አለው።

በቀጣይ ምዕራፎች በ20 ሄክታር መሬት ላይ የደረቅ ወደብ የሚገነባ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ሥራው ሲጠናቀቅ እስከ 9 ሺህ 450 ኮንቴነሮችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል። ደረቅ ወደቡ በዓመት 95 ሺህ 800 ኮንቴነሮችን የማስተናገድ አቅም እንደሚኖረው ይታመናል።

LEAVE A REPLY