ብልፅግና ፓርቲ በ40 ሚሊዮን ብር አዲስ ጽ/ቤት ሊገነባ ነው

ብልፅግና ፓርቲ በ40 ሚሊዮን ብር አዲስ ጽ/ቤት ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብልፅግና ፓርቲ በጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባለሦስት ወለል የጽሕፈት ቤት ሕንፃ ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ።

በያዝነው ዓመት የሚጀመረው የሕንፃው ግንባታ በቀጣዮቹ  ኹለት ዓመታት የሚጠናቀቅ ሲሆን የፓርቲው የዞን ኃላፊዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ቢሮዎች፣ ሦስት አዳራሾች እና መዝናኛ ክበቦች እንደሚኖሩት ተነግሯል።

የግንባታው ወጪ የፓርቲውን ዓላማ እና ሐሳብ በሚደግፉ የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት ድጋፍ እና ሀብት በማሰባሰብ ለመሸፈን መታቀዱን የጠቆሙት የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት  ቤት ኃላፊ  ፀሐይ ወራሳ የክልሉ መንግሥትም የተወሰነ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY