ነገ የሚጀምረው ጨፌ ኦሮሚያ ጉባዔ የፀጥታ ችግር ላይ ያደርጋል ተባለ

ነገ የሚጀምረው ጨፌ ኦሮሚያ ጉባዔ የፀጥታ ችግር ላይ ያደርጋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ነገ የሚጀምረው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባዔ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰው በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚመክር ተነገረ።

የጨፌው አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ጨፌው ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ ለጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደነበር አስታውሰው፤ ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ሰላማዊ ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል። ይሁን እንጂ አሁንም ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ ጨፌው እንደሚሠራም አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የተከናወኑ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ባሉት ቋሚ ኮሚቴዎች ሲገመገም እንደነበር የጠቆሙት አፈ ጉባዔዋ፤ በዚህም የአስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ታይቶ ግብረ መልስም ተሰጥቷል ብለዋል።

ጨፌው የተሰጠው ኃላፊነት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ማጠናከር እንደመሆኑ ከአጎራባች ክልል ሕዝቦች ጋር በቅርበት ተርቷልም መባሉን ሰምተናል:: ነገ በሚጀምረው ጉባኤ የስድስት ወራት የክልሉ መንግስት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል። በጉባዔው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችም ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ይፀድቃሉ ተብሎ ከወዲሁ በመነገር ላይ ነው::

LEAVE A REPLY