ኤጄቶ የሲዳማ ርክክብ ከየካቲት 15 ካለፈ አመጽ አስነሳለሁ ሲል አስጠነቀቀ

ኤጄቶ የሲዳማ ርክክብ ከየካቲት 15 ካለፈ አመጽ አስነሳለሁ ሲል አስጠነቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  የንጹሃንን ደም በማፍሰስ የሚታወቀው ኤጄቶ ዳግም ለአዲስ ግጭትና ጥፋት በስውርና በይፋ መንቀሳቀስ ጀምሯል።

በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ሰበብ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በተለያዮ የሲዳማ ዞን ከተሞች ዘግናኝና አሳፋሪ ጥቃት የፈጸመው ኤጄቶ አሁን ላይ ለሌላ ጥቃት ራሱን እያደራጀ እንደሚገኝ የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በቅርቡ በሪፈረንደም ውሳኔ ያገኘው የሲዳማ ጉዳይ እስከ የካቲት 15 ቀን የሥልጣን ርክክብ ተካሂዶ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስረታ የማይካሄድ ከሆነ ኤጄቶ (የሲዳማ ወጣቶች ቡድን) ተቃውሞ እንደሚያስነሳ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

መንግሥት ከሕዝቡ የሚተላለፉትን ጥሪዎች በቸልታ የሚያልፍበት መንገድ የሚመጡትን ችግሮች ከማባባስ በቀር ወደ መፍትኄ የሚያቀርብ አማራጭ ሊሆን እንደማይችል የጠቀሱት ስማቸውን የደበቁ የኢጄቶ አባል መንግሥት በአብዛኛው ኅብረተሰብ ተቀባይነት ያገኘውን ውሳኔ ላለማስፈጸም አማራጭ እያፈላለገ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

የደቡብ ክልል አመራሮች የሥልጣን ርክክቡን ለማዘግየት እየጣሩ እንደሆነ እና ለሲዳማ አመራሮችም ሕዝቡን እንዲያሳምኑ አጀንዳ ተሰጥቷቸዋል ያሉት የኤጄቶ አባላት እስከ የካቲት 15 ድረስ መንግሥት የሥልጣን ርክክቡን የማያደርግ ከሆነ አደባባይ እንደሚወጡ ይፋ አድርገዋል::

ቀደም ሲል በ11/11/2011 የተፈጠረውን ደም መፋሰስ በክፉ ጎኑ ያስታወሱት የኤጄቶ አባላት አሁንም ለሚመጣውና ለሚከሰተው ነገር ሁሉ ዋነኛ ተጠያቂ የሚሆነው መንግሥት ነው ሲሉ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY