ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት ለመጠቀም ሲባል ከውጪ አገራት ሲገባ የቆየው የድንጋይ ከሰል ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ሊደረግ መሆኑ ተሰማ::
ከውጪ አገራት የሚመጣውን የድንጋይ ከሰል ምርት ማቆም ያስፈለገው ኢኔዱስትሪዎች በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ እንደሆነም መረጃዎች ይጠቁማሉ::
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደስ ኃይለማርያም ከሰል ድንጋይ ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ሥራ በሚመሩት መንግሥታዊ ተቋም በኩል ሲፈጸም መቆየቱን አስታውሰው የማዕድን የነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ከውጪ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ለመተካት እንዲሁም የከሰል ድንጋዮ ባለው ኬሚካላዊ ይዘት ላይ ጥናት በማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል::