- || ዳግማዊ ጉዱ ካሣ ||
“ሀገር እየታመሰች አንተ ስለድራፍት ዋጋ መጨመር ታወራለህ፤ የደላህ ነህ!” እንዳትሉኝ እንጂ የአቢይ መንግሥት ድል በድልእየተምበሸበሸ መጥቶ አሁን ደግሞ ባለችን አንዲት መዝናኛ ላይ ውኃእማያሰኝ ዱላውን አንስቷል፡፡ የፕሮቴስታንቶቹ መንግሥት አልቻልብሏል፡፡ አብዛኞቹ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከመጠጥ ጋርያላቸው ፍቅር እስከዚህ መሆኑ ይነገራል – ቢያንስ ሲጠጡ በአደባባይአይታዩምና፡፡ እዚህ ላይ “ውስጡን ለቄስ” የሚሉ ወገኖች እንዳሉ ግንአይካድም፡፡ ታላላቅ ፓስተሮች ሳይቀሩ በቤታቸውና በሥውር ዝጉብኞችበውስኪና በቢራ እንደሚራጩ የሚወራ መሆኑን መደበቅተሸኮርማሚነት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ሰው በወደደው ይቆርባልና በዋጋጭማሪ የሰውን ፍላጎት ለመግታት መሞከር ነውር ነው፡፡
ትናንት ማታ እንደወትሮየ ከሥራ ወጥቼ ሱክ ሱክ እያልኩ ጓደኞቼወደሚገኙበት የማታ ትምህርት ማዘውተሪያ ሥፍራየ እሄድላችኋለሁ – ለእናንተ ስል መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ እንደደረስኩ የቀደሙኝ ጓደኞቼ “ዳጊየምሥራች!” ይሉኛል፡፡ ምን ተገኝቶ እንደዚያ እንዳሉኝ ሳልጠይቅ“ምሥር ብሉ!” እላለሁ፡፡ አንዱ ለጠቀና “ያን የተለጠፈ ወረቀትአንብበው” ይለኛል፡፡ ሳነበው በዚያ የሕዝብ መዝናኛ የቀበሌ ክበብ 13 ብር የነበረው ድራፍት አምስት ብር ጨምሮ 18፣ 15 ብር የነበረው ትንሹጠርሙስ ቢራ 20 ብር መሆኑን እረዳለሁ፡፡
እውነቴን ነው የምላችሁጠላታችሁ ክው ይበልና እንደሎጥ ሚስት ክው ብዬ ቁሜ ቀረሁ፡፡ ቁጭ እንድል ቢወተውቱኝም የሀዘኑ ብዛት ወደ ተረጋጋ ሰውነቴሊመልሰኝ አልቻለም፡፡ ሌላ ብሶታችንን የምንተነፍስበት ነገር የለንም፡፡ ከየትም ተሰባስበን ካለችን አነስተኛ ገቢም ቆንጥረን ቤተሰባችንንበመበደል የሆድ የሆዳችንን ተንፍሰን ወደየጎጇችን የምንገባው በዚሁድራፍትና ቢራ ነበር፡፡ በዚህም መጡብን፡፡ አምባገነኖችየማይመጡብህ አቅጣጫ የለም፡፡ አሁን የቀራቸው ባል ከሚስቱ፣ ሚስትም ከባሏ ለምታገኘው ተፈጥሯዊ እርካታ ግብር ማስከፈል ብቻነው፡፡ እንደዚያ ቢሉኝ ሲፈልጉ ያስመርምሩኝ እንጂ “የሜተር አርቲስትአፈወርቅ ተክሌ ወንድም ከሆንኩ ሰነበትኩ!” ነው የምላቸው፡፡ ሆ! ሰው“በገዛ መንግሥቱ” እንደባብ እየተቀጠቀጠ ተሳቅቆ ይኖራል? ምንዓይነት ውርጅብኝ ነው! በሣዳም ሁሴንና በጋዳፊ የወረደው መቅሰፍትበነዚህም ላይ ይውረድ፤ አሜን! የተባረኩ መንግሥታት ቀጭን ሰበብእየፈለጉ ሕዝባቸውን ይጠቅማሉ፡፡ ከድህነት ሠፈር የመጡ የኢትዮጵያመሪዎች ደግሞ ድህነት አንጎላቸው ውስጥ ቤቱን ስለሠራባቸውበህልማቸውም በእውናቸውም የሚያስቡት ስለማደህየት እንጂስለማክበር አይደለም፡፡ እናም ዕረፍት አጥተው የሚጨነቁት ሕዝብንስለማቆርቆዝና አቆርቁዞም ስለነሱ እንዳያስብ ማድረግ ሆነ፡፡ በነሱ ተራየፖለቲካ አስተሳሰብ ሕዝብ ከተመቸው ለመንግሥት አይመችም ነው፡፡ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን፡፡
እርግጥ ነው መጠጥ ለማንም አይመከርም፡፡ መጠጥ ገዳይ ነው፡፡ ገዳይነቱ ግን በአወሳሰድ ይወሰናል፡፡ በልክ ከሆነ ደግሞ ያጫውታል፤ ሀዘን ትካዜን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ያስረሳል፡፡ በዚያም ላይ ጓደኝነትንያጠናክራል፤ ሰውን ያቀራርባል፤ ያወያያል – የዚህ ጭማሪ ዓላማም ይህንለማስቀረት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ጉዳት ብቻ ሳይሆን ጥቅምምአለውና በዚህ ማኅበራዊ ገመድ ላይ ይህን ያህል መጨከን የጤናአይመስልም፡፡
አንድ ጭማሪ ሲደረግ ጥንቃቄን ይሻል፡፡ የዱሮ ጭማሬዎችንስናስታውስ የሚገርሙ ነበሩ፡፡ ሥንትና ሥንት ዓመት ቆይቶ የሚደረግጭማሪ ቢበዛ አሥር ሣንቲምና አሥራ አምስት ሣንቲም ነው፡፡ አሁንግን የዛሬ 30 ዓመት ገደማ 1.70 ሣንቲም የነበረ ድራፍት አሁን በሕዝብመዝናኛ ክበብ ብቻ ብር 18 ሲገባ ጭማሪው ዘግናኝ ነው፡፡ በመቶኛብትመቱት እጅግ ብዙ ነው፡፡ በአንድ ቢራ አምስት ብር መጨመርየጨማሪውን የቁጥር ችሎታ ገደል የሚከት ነው፡፡ ሃምሣ ሣንቲምመጨመር ወግ ነው፤ አንድ ብር መጨመርም ወግ ነው፤ አምስት ብር?! በግል ቡና ቤቶች ደግሞ “እንኳን ዘምቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ”እንዲሉ ናቸውና ይሄኔ ሰማይ ሰቅለውታል፡፡ ሌባው በዛ፤ ደህናው አነሰ፤ በኑሮ እየተገረፈ ያለው ደህናውና የወር ገቢው ለሁለት ቀናትምየማይበቃው ዜጋ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ወዴት አለህ?! እባክህንሕዝብህን አስብ፣ ርስትህንም ባርክ፡፡
ለነገሩ ከፕሮቴስታንት ምን ይጠበቃል? ባለሥልጣኑ ሁሉ ከላይእስከታች ጴንጤ ወይም ሙስሊም ነው፡፡ እነዚህ ባለሥልጣናት ደግሞከኛ ጋር ወርደው ድራፍትና ቢራ አይሻሙም፡፡ ከፈለጉ ምን የመሰለምርጥ ሻምፓኝና ዊስኪ ከሎንዶን ቤታቸው ድረስ በቀጥታይመጣላቸዋል፡፡ ይህ ጨለማ የማይነጋ እየመሰላቸው ግና በኛ በድሆችላይ ጢባጢቤ ይጫወታሉ፡፡ ለማየት ያብቃችሁ – አያያዛቸው ሁሉሌሊቱን የሚያሳጥር ነውና ተስፋችንን በአንድዬ ጥለን ከኃጢኣትናከክፋትም ተቆጥበን የምንችለውን ሁሉ እናድርግ፡፡ ወሮበሎች ጋርአንተባበር፡፡ ደግሞም በርትተን እንጸልይ፡፡
በሶቭየት ኅብረት ዘመን ራሽያዎች ድንችና ቮድካ ርካሽይደረግላቸው ነበር፡፡ ያን ካገኙ ወደ መንግሥት አያስቡም፡፡ መጽሐፉምእኮ “ድሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ የወይን ጠጅ ስጡት” ይላል፡፡ ጴንጤዎቹመሪዎቻችን ግን ይቺን ጥቅስ አላነበቧም መሰለኝ፡፡ እንዲህ በአራቱምማዕዘን አክረው አክረው የተበጠሰ እንደሆነ (መበጠሱም አይቀርም) እነሱን አያድርገኝ፡፡ አቢይ ከመጣ ወዲህ ኑሮው ከቀን ወደ ቀንእንደመንኮራኩር እየተወነጨፈ ነው፡፡ እርሱ ግን ምንምአልመሰለውም፡፡ የአንድ ሽህ ምናምን ብር ኩንታል ጤፍ አራት ሽህሲገባ አቢይን ስለማይርበው ቅንጣት አላሳሰበውም፡፡ የሃያ ብሩ የምግብዘይት 80 እና 90 ሲገባ የርሱ ምግብ በሕዝብ ቅቤና ዘይት ስለሚሠራጉዳዩ አይደለም፡፡ ወይ መንግሥት መሆን! በኢትዮጵያ መንግሥትመሆን እንዲህ ልበ-ድፍን ያደርጋል ማለት ነው? የነሱ ከርስ አይጉደልእንጂ ስለሕዝቡ የዕለት ከዕለት ኑሮ እኮ ቅንጣት አያስቡም፡፡ እነዚህንየአጋንንት ልጆች ከየትኛው የሲዖል መንደር አፍሶ እዚህች ኢትዮጵያውስጥ እንደዘረገፈብን እሱ ራሱ ይወቅ፡፡ ይሄ ሁሌ ይገርመኛል፡፡
ሀገር ቁና ሆናለች፡፡ ኑሮ ወደሰማየ ሰማያት በብርሃን ፍጥነትተተኮሰ፡፡ በዚህ የመጠጥ ዋጋ ጭማሪ ደግሞ ለማየት ያብቃችሁሕይወት እንደኳስ ሽቅብ ትጉናለች፡፡ እያንዳንዱ የግል ተዳዳሪ ይህንየመጠጥ ውድነት ለመጋፈጥ ሲል በሚሸጠው ዕቃና በሚሰጠውአገልግሎት ላይ ዋጋውን ዕጥፍ ድርብ ሲያደርገው ነገሩ ሁሉ ቡሃ ላይቆረቆር ይሆናል፡፡ ይህን የሚፈልጉ አምስተኛ ረድፈኞች ሳይሆኑአይቀሩም በዚህ የቀውስ ሰዓት በአላስፈላጊ ሁኔታ ይህን የዋጋ ጭማሪእውን ያደረጉት፡፡ አለበለዚያማ ሀገር በብዙ ችግሮች እየተናጠች፣ የኑሮውድነቱ በተለይ ቅጥር ሠራተኛውን ከመኖር ወዳለመኖር እየለወጠውበሚገኝበት በዚህ አስጨናቂ ወቅት ይህን ያህል እጅግ የተጋነነ ጭማሪአይደረግም ነበር፡፡ በአንዲት ብርጭቆ አምስት ብር መጨመር ማለትበራሱ እስካሁን በፍጹም ኪሣራ ነበር የሚሠሩት ማለት ነው፡፡ እንዲያእንዳልሆነ ደግሞ እናውቃለን፡፡
ለማንኛውም በዱሮው አጠራር የመላው ኢትዮጵያ ጠጭዎችማኅበር አባላትን በዚህ አጋጣሚ “እግዜር ያጥናችሁ፤ የጌሾ ጌታችግራችሁን ይስማችሁ” በማለት ላጽናናችሁ እፈልጋለሁ፡፡ እኔስ ዕድሜለቁንድፍት ወደታችኛውና ወደሚያዋጣኝ መንደር ጎራ እላለሁ – እሷምየወቅቱን ፋሽን ተከትላ አሁን ካለችበት በመለኪያ አራትና አምስት ብርወደ ስምንትና ዐሥር ብር ልወርወር ካላለች፡፡ ተለያየን!