“የስልጤ ሕዝብ መነሻው ስልጤ፣ መድረሻው ዓለምነው” ሲሉ ዶ/ር ዐቢይ ተናገሩ

“የስልጤ ሕዝብ መነሻው ስልጤ፣ መድረሻው ዓለምነው” ሲሉ ዶ/ር ዐቢይ ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሌሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋራ በመሆን በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ ስቴዲየም ከተለያዩ የዞኑ አከባቢዎች ከተሰባሰቡ 60 ሺህ እስከ 65 ሺህ የሚደርስ ሕዝብ ጋራ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወራቤ ስቴዲየም ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደረጉት ንግግር የስልጤ ሕዝብ በመላው ገሪቱ ተሰማርቶ ገር በመልማት የሚታወቅ ታታሪ ሕዝብ ነው ብለዋል፡፡ የስልጤ ሕዝብ ዜግነት ወንዝ መሆኑን ያውቃል፡፡ ስልጤ መነሻው ስልጤ መድረሻው ዓለ ነው፡፡ አስቀድሞ የስልጤ መንገድ የመደመር ነው መንገዱ ደሞ ከመስመር ይሰፋል፡፡

እኛ ጠባቡን መስመር ትተን ሰፊውን መንገድ ተከትለናል፤ በመረጥነው መንገድ ወደ መድረሻችን በልፅገን ለመሄድ አንደክምም፣ አንተኛም።  የማንተኛው ዕዳ ያለበት ገር ስለተረከብን ነው፡፡ ባለዕዳ ማውራት ዕዳ መከፈል አይደለም የተሻለችና ከዕዳ የነፃች ገር ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንተጋለን።”  ብለዋል። 

የስልጤ ሕዝብ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉት እናውቃለን ተደምረን ጥያቄዎች ደረጃዎች በደረጃ ለመፋታት እንሰራለን

የኢትዮጵያ ሠላምና አንድነት አብሮነት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድነትና አብሮነት በመጠበቅ ስም ታዳጊዎች የጦር መሳሪያ መሸከም ስለጦረኝነት ማስተማር ነው፡፡ ስለሆነም ለልጆቻችን ክላሽ ሳይሆን ስክሪፕቶና እርሳስ ሐፍ ቅዱስ እና ቁራን  እንጂ የጦር መሳሪያ አናሸክማቸው ሲሉም ዶክተር ዐቢይ አገርና ትውልድን ከጥፋት የመታደጊያውን መንገድ አመላክተዋል፡፡  

LEAVE A REPLY