የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ልዮ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ተባለ

የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ልዮ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገ ባለድርሻ አካላትና የክልል መስተዳድሮች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች የሴቶች ወጣቶችና ማኅበራ ጉዳዮችቋሚ ኮሚቴ የኢንስቲትዩቱን የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ በሽታው ከጉንፋን ቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቢሆንም 14 ቀናት ውስጥ ሳል ንጥሻ፣ የትንፋሽ ማጠርና የጉሮሮ ሕመም ምልክቶች የሚያሳይ ሲሆን ይህም በሽታው በፍጥነት አንዲዛመት ያደርጋል ሲሉ ለጎብኚዎቹ አስረድተዋል፡፡

ዳይሬክተሩና አያይዘውም ቦሌ ጨፌ ኢቦላ ማዕከል የካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታልና ቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልአገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ መሆናቸውን ጠቁመውነገር ግን በሁሉም የአገሪቱ  ክፍል የመሸፈን አገልግሎት ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቫይረሱ ወደ አገር እንዳይገ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ የሚመለከታቸው አካላት እና 150 በላይ ባለሙያዎች ያካተተድንገተኛ ማዕከል በቅንጅት እየሠ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ከቻይና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች ለምርመራ ፈቃደኛ ባመሆናቸው የፀጥታው ኃይል ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ዶክተር ኤባ አባተ ተናግረዋል፡፡  

LEAVE A REPLY