“ጆርኒ ቱ ዴዝ” የተሰኘው የጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

“ጆርኒ ቱ ዴዝ” የተሰኘው የጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በረካታ ውጣውረዶችን ያሳለፈው የቃልኪዳን መጽሔት እና የሞገድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እንዲሁም በበርካታ ጋዜጦች ላይ በአዘጋጅነት ሰፊ ተሳትፎ የነበረው፣ አሁን በስደት በአሜሪካ የሚገኘው ዳንኤል ገዛኸኝ የተፃፈው መጽሐፍ በአማዞን ላይ ለሽያጭ መቅረቡ ተገለፀ፡፡

1997 ምርጫን ተከትሎ ወደ የመን በባህር ላይ አደገኛ ጉዞ በማድረግ የተሰደደው ዳንኤል ገዛኸኝ 72 ሰዓታት ሰሀራ በረሃና 41 ሰዓት በቀይ ባህር ላይ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካይነት ያያውን ስቃይና እንግልት የተረከበት ሲዋን የተባለ በአማርኛ ቋንቋ የታተመ መጽሐፉ ነው ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ጆርኒ ዴዝ የተሰኘ ርዕ ተሰጥቶ ለኅትመት የበቃው፡፡

ደራሲው ለኢትዮጵያ ነገ የአዲስ እንዳስታወቀው መጽሐፉን 11 ዶላር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም በመግዛት ለሚያደርገው የኩላሊት ንቅለተከላ kidney transplant  ኢትዮጵያውያን ወገናዊ እገዛ እንዲያደርጉለት ተማፅኗል፡፡

LEAVE A REPLY