ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የነዳጅ ድፍድፍ ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ምንነቱ ባልታወቀ ሕመም ሕይወታቸው እንዳለፈ እና ጉዳት እየረደሰባቸው መሆኑን ዘጋርድያን አስታወቀ።
የቻይናው ፖሊ ሲ ጂ ኩባንያ በአካባቢው የድፍድፍ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፍልጋውን ከጀመረ በኋላ ይህ ዓይነቱ ክስተት መስፋፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአባቢው ነዋሪ የነበረው ከድር አብዲ አብዱላሂ የተባለ የ23 ዓመት ወጣት ፤ በመጀመሪያ አይኖቹ እና የእጆቹ መዳፍ ቢጫ ሆነው ነበር ሲል ያስረደው ዘገባ በቀጣይ ከአፍንጫውና ደም ይፈሰው እንደነበር በመግለፅ በኋላም ሕይወቱ ማለፉን አስታውቋል።
በፌደራል መንግሥትም በኩልም ምክንያቱ የጤና ችግር ይሁን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር የለም ነው ያሉት አካባቢው ነዋሪዎች። ነገር ግን የከድርን ሞት ጨምሮ ምክንያት ሊሆን የሚችለው አካባቢው ላይ ባለው መርዛማ ኬሚካል ውሃዎች ተበክለው ሳይሆን አይቀርም ሲሉ እነዚህ የአካባቢው ነዋሪዎች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ከሃዳር የተባለው የጅግጅጋ አካባቢ ነዋሪ በበኩሉ አካባቢው መርዛማ ኬሚካል ያለበት ነው እኔም በቅርቡ ከሆስፒታል የወጣው ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች ምን ሊያደርጉልኝ አልቻሉም ሲል ተናግሯል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የሶማሌ ክልል አማካሪ በበኩላቸው ” ከዚህ በፊት እንዲህ ዓይነት በሽታ ታይቶ የአይታወቅም፣ ይህ አዲስ ክስተት ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ የአካባቢው ሕዝብ ምንም የጤና ጥበቃ ሳይረግለት የፖሊ ጂሲኤል ኩባንያ የሚጠቀመው ኬሚካል ሰዎችን ሊጎዳ እንሚችል መታወቅ አለበት ሲሉም አክለዋል።
የፖሊ ጂሲኤል ኩባንያ አስተያየት ከመስጠት እንደተቆጠበ ዘ ጋርዲያን በዘገባው አመላክቷል።
የኢፌዲሪ የማዕድን፣ፔትሮሊየምና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ቀጸላ ታደሰ በመንግሥት በኩል ነገሩን እንደማያውቀው በመለግለፅ ፣ የነዳጅ ክምችት ባለበት ቦታ ላይም ቋሚ ሰፋሪ ሰዎች የሉም በማለት ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ አካባቢው ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳያደርስ ዓለም ዐቀፍ ደረጃን ተከትሎ የተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በፈረንጆቹ ከ2014 ጀምሮ እስካሁን ወደ 2000ሺህ ገደማ ሰዎች ሕይታቸው ማለፉን ዘ ጋርዲያን ይፋ አድርጓል።ፖሊጂሲኤል ፔትሮሊየም ኢንቨስትመንት የተባለው የቻይና ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ2013 ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር የነዳጅ ልማት ስምምነት የተፈራረመው ሲሆን ፣ ከ2014 ጀምሮ የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝ ፍለጋ ሥራ ሲያከናውን መቆየቱም ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኩባንያው በምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሲያደርግ የቆየው የድፍድፍ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ውጤት ማስገኘቱን እና ሙከራ መደረጉን ሰኔ 21/2012 መግለጻቸው ይታወሳል፡፡