ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አቶ አሸብር በቀድሞ የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በሜካኒካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የተቀበሉ ሲሆን፤ ከብሪታንያ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በዓለም ዐቀፍ ቢዝነስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
ግለሰቡ በምህንድስና ከተመረቁ በኋላም በበደሌ ቢራ ፋብሪካ ጀማሪ ሜካኒካል ኢንጂነር የሥራ መደብ ላይ አገልግለዋል።
በ1996 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቀጥረው በጊምቢ –መንዲ – አሶሳ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ሠርተዋል። በተጨማሪም በተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከጥር 1997 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ዓመት መሪ መካኒካል ኢንጂነር ሆነው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በመቆጣጠር ተቋሙን አገልግለዋል።
ከግንቦት 2003 ዓ.ም ጀምሮ የጊቤ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ኃላፊነት እስከተቀበሉበት ቀን ድረስ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል።