ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሀዋሳና ቢሾፍቱን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሥራ በመደገፍ የተለያዩ የድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ።
በሀዋሳ ከተማ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይ በርካታ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እና የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ የድጋፍ ሰልፉ ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድንና ብልፅግና ፓርቲን እንደግፋለን፣ ብልፅግና ፓርቲ ለአገራችን ህልውና እና ለህዝባችን ህይወት መሻሻል ያለውን ራዕይ እንደግፋለን፣ ለውጡን ሊቀለብሱ የሚፈልጉ ኃይሎችን እንቃወማለን” የሚሉ እና ሌሎች ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ለብልፅግና የድጋፍ ሰፍል አድርገዋል። በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙት ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በተለያዮ መንገዶች ገልጸዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ “ብልፅግና ለሁሉም፤ ሁሉም ለብልፅግና፣ ስድብ የኦሮሞ ባህል አይደለም፣ ከዶክተር ዐቢይ ጎን መሰለፍ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ነው፣ በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር፣ አንድነት ለሰላምና ለብልፅግና” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
የጉጂዞንነጌሌከተማእናየአካባቢውነዋሪዎችበዛሬውእለትባካሄዱትሰልፍለጠቅላይሚኒስትርዐቢይአሕመድእናለብልፅግናፓርቲያላቸውንድጋፍገልፀዋል።በድጋፍሰልፉላይየተካፈሉሰዎችጠቅላይሚኒስትርዐቢይአሕመድወደስልጣንከመጡወዲህየሠሯቸውሥራዎችተጠናክረውእንዲቀጥሉባላቸውእውቀትእናአቅምድጋፍእንደሚያደርጉምተናግረዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች በአገሪቱ እየተካሄደ ያለውን የለውጥና የብልጽግና ፓርቲን በመደገፍ ሰልፍ ያካሄዱ ሲሆን፥ በሰልፉ ላይ የፍቼ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ ከዞኑ 13 ወርዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።ነዋሪዎቹ በፍቼ ስታዲየም በመገኘት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን እንደሚደግፉ እና ለብልጽግና ፓርቲም ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።
በባሌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልፅግና ፓርቲ ድጋፍ የድጋፍ ሰልፎች ተካሂደዋል። በሰልፎቹ ላይም “ኦሮሞ በማንኛውም ሴራ አይበታተንም፣ የህዝብ ተጠቃሚነት በፍላጎት እና በምኞት ብቻ ከግብ አይደርስም፣ በሃይማኖት እና በብሄር ሊከፋፍለን የሚፈልጉ ኃይሎች ቦታ የለንም፣ ዶክተር ዐቢይ ሁሌም የኦሮሞ ህዝብ ከጎንህ ነው፣ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ቀጣይ ጊዜ ብሩህ ነው እና ይቅርታ፣ ፍቅርና ብልፅግና ነው የሚያሻግረን” የሚሉ መልእክቶችን ተላልፈዋል።