ግብጽ:-“አሜሪካ ስለ ህዳሴው ግድብ ሀሳብ ታቀርባለች…” || ታምሩ ገዳ

ግብጽ:-“አሜሪካ ስለ ህዳሴው ግድብ ሀሳብ ታቀርባለች…” || ታምሩ ገዳ

ግብጽ:-“አሜሪካ ስለ ህዳሴው ግድብ ሀሳብ ታቀርባለች…”

ኢትዮጵያ በአምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች በሚገኘው ግዘፉ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የአሜሪካ መንግስት “የማግባቢያ ረቂቅ ሐሳብ ሊያቀርብ “መባሉ ከወደ ግብጽ ተሰማ።

የግብጹ ደይሊይ ኒውስ ኢጂፕት /Daily News Egypt/ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተሩ ሳሚ ሽኩሪይን ጠቅሶ በትላንትናው እለት እንደዘገበው” በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በቅርቡ የተካሄደውን ድርድር ተመርኩዞ የአሜሪካ መንግስት አግባብነት ላላቸው ለግብጽ፣ለኢትዮጵያ እና ለሱዳን መንግስታት የመጨረሻውን ረቂቅ ሀሳብ በቀጣዩ ሳምንታት ያቀርባል”ብለዋል። በታዛቢነት መሰየሟ የተነገረላት አሜሪካ ምን አይነት የመግባቢያ ሀሳብ ይዛ እንደምትመጣ ሽኩሪይ በግልጽ አላብራሩም።

ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ማክሰኞ ኢትዮጵያን የጎበኙት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ማይክ ፓምፖዬ የህዳሴው ግድብን በተመለከታ አዲስ አበባ ላይ በስጡት አስተያየት ” ከፊታችን ትልቅ ስራ የተደቀነ ቢሆኑም ፣በህዳሴው ጉዳይ ያሉትን ችግሮችን በቀጣዩ ወራት ከእልባት እናደርሳልን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ”ብለዋል።

የ ሶስትዮሹ ድርድር ተሳታፊ የሆነችው ሱዳን በበኩሏ ከአሜሪካ እና ከአለም ባንክ ረቂቅ የመግባቢያ ሰነድ አግኝታለች መባሉን በተመለከተ ምላሽ የሰጠች ሲሆን
የአገሪቱ የመስኖ እና የውሃ ሚኒስተር የሆኑት ፕሮፌሰር ያሲር አባስ ለዜና ሰዎች በሰጡት አስተያየት”ከአሜሪካኖቹ በኩል ያገኘነው ነገር ቢኖር ዘላቂ መፍትሔ የሚያመጣ የቴክኒካል እገዛ ነው”በማለት ከአለም ባንክ እና ከአሜሪካ ቀርቧል የተባለውን “ረቂቅ የመግባቢያ “ሰነድ ጉዳይን አስተባብለዋል።

ምንም እንኳን የህዳሴው ግድብ ድርድር ዙሪያ የአለም ባንክ እና የአሜሪካ ተሳትፎ ከታዛቢነት ያልዘለለ እንደሆነ ባለስልጣናት በተለያዩ ጊዜያት ቢያስተባብሉም በርካታዎች ኢትዮጵያኖች በወንዙ ላይ ከነበራት የልማት ግስጋሴዎች ከግብጽ ባሻገር ሲደርሱባት ከነበሩ ውጫዊ ጫናዎች አኳያ የ ጥርጣሬ መንፈስ በውስጣቸው እንደገባ ይናገራሉ።

በተያያዘው የአባይ ወንዝ ዜና ነገ ቅዳሜ የካቲት /ፌበርዋሪ 22,2020 እኤአ ሱዳን የአባይ ቀን/The Nile Day/እንደ ምትከ ብር ፕ/ር ያሲር ለዜና ሰዎች በሰጡት መግለጫ ላይ የገለጹ ሲሆን ይህ ካርቱም ለሁለተኛ ጊዜ የምታስተናግደው የአባይ ቀን በተመለከተ” ሁሉም የተፋሰሱ አገራት የሚሳተፉበት፣ በጋራ ለመስራት ፣ለመልማት ቃል የሚገቡበት፣ ከአምስት መቶ በላይ እንግዶች የሚታደሙበት በአይነቱ የመጀመሪያው ይሆናል”በማለት ምኞታቸውን ገልጸዋል። በካርቱሙ የአባይ ወንዝ ቀን የየአገራቱ የው/ጉ/ሚ/ር ፣የግብርና፣ የኤሌክትሪክ ፣የአካባቢ፣የመስኖ፣የህዝብ እንደራሴዎች ተወካዮች እና አግባብነት ያላቸው ባለስልጣናት እና እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY