ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የቡራዩ ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሚሽነር ሰለሞን ታደሰ ትናንት ምሳ ሰዐት ላይ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል፡፡ እስከሁን ሃላፊነቱን የወሰደ የለም። እስከሁን 17 ሰዎች መያዛቸው ታውቋል። ሰዎች ግድያውን ያቀነባበሩ ናቸው ተብሏል።
የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ እንደገለጹት ከሆነ በቡራዩ ከተማ በደረሰው ጥቃት የከተማዋ አስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሚሽነር ሰለሞን ታደሰ ህይወታቸው ያለፈው በአንድ ሆቴል ውስጥ ምግብ እየተመገቡ ባለበት ወቅት ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ነው፡፡
በታጣቂዎቹ ጥቃቱ ሲፈጸም በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የልዩ ኃይል አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ዲንቁን ጨምሮ በሦስት ሰዎች ላይ የመቁሰል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከግለሰቦቹ መሀል አንዱ ድምጻዊ ደረጀ ጃለታ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ቡራዩ ዶክተር አብይ ስልጣን ከጨበጡበት እለት አንስቶ በርካታ የፖለቲካ ትኩረት የሳበች ከተማ ስትሆን ዘግናኝ ብሔር ተኮር ግድያን ጨምሮ ወታደሮች ወደ ቤተመንግስት ያማሩበት ትእይንት የተስተናገደው ከቡራዩ የተጀመረ ሲሆን ባለፈው በአንድ የሆቴል ምረቃ ላይ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውም ይታወሳል።