ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት ልዑክ ከግብፁ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያየ

ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት ልዑክ ከግብፁ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያየ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ልዩ ልዑክ ከግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ጋር ተገናኝተዋል።

በልዮ ሁኔታ በተዋቀረው ልዑካን ቡድኑ ውስጥ የተካተቱት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እና በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ናቸው።

አቶ ኃይለማርያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከንም መልዕክት ለፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል ከመባሉ ውጪ ምንም የተብራራ እና ግልጽ የሆነ መረጃ እስካሁን አልተሰጠም።

ልዑኩ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበረው ቆየታው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያየቱን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

LEAVE A REPLY