እቴጌ ጣይቱ አዲስ አበባ የሚለውን ስያሜ እንደሰጧት የሚነገርላት ከተማ ሁልጊዜ እንዳበበች፤ መዓዛዋም እንዳወደን ይገኛል። ሊያጠፏት ሴራ ሲሸረቡ፤ ሰላሟንናፍቅሯን ሊነሷት ቢዶልቱባትም ታሪክ እየሰራች ከመጓዝግን አልቦዘነችም።
አዲስ አበባ የሁላችን ከተማ፤ የአፍሪካና የዓለም መዲና በመሆኗበቀላሉ አትጠፋም። ከተማዋ የተቆረቆረችውና የተመሰረተችው በጠንካራ ኢትዮጵያዊ አርበኞች፤ ምሁራን፤ መሐንዲሶች፤ ሐኪሞች፤ አርቲስቶች፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ የእምነት አባቶች፤ ነጋዴዎችና ፖለቲከኞች ነው። መስራቾቿን ወልዳ፤ በየፈርጁ አስተምራና አሳድጋ አቋቁማለች፤ ለወግ ለመአረግ አብቅታለች። ልጆቿ ከአስራ አራቱም ክፍለ ሃገራት ወይም ጠቅላይ ግዛትና ከሌሎች ዓለማት ጭምር መጥተው የተማሩባት፤ የነገዱባት፤ የሰሩባት፤ የበለጸጉባት፤ ትዳር የመሰረቱባት የሁሉም ከተማመሆኗ ሊታወቅ ይገባል።
መሐሙድ አሕመድ አዲስ አበባ ቤቴ ብሎ ያንጎራጎረላት፤ ቲወድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮን) የመሰለ አዲስ ትውልድ ከያኒያፈራች የግብረገብ ከተማ ነች። በዚህና መሰል በሐሪዋ አዲስአበባ እንደ ኒዮርክ፤ ሎንዶን፤ ናይሮቢ፤ ቶሮንቶ፤ ዋሽንግቶንወዘተ ሁለገብ ከተማነቷን (Cosmopolitan City) መካድ ከቶአይቻልም።
አዲስ አበባ ፍቅር እንጂ ዘር፤ ጎሳ፤ ቀለምና ጎጥ አታውቅም። ከአብሮነት ውጪ የመነጣጠል ትርክት አይገባትም። ይህንምቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2012 በቴዲ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይነዋሪዎች በአንድ ድምፅ መስክረዋል። ነዋሪዎቿ የሚያውቁት ሶስት ቀለማትን ማለት አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሲሆን ዘሯም ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።
በከተማዋ ተወልዶ ያደገው የኪነት ባለሙያ ቴዲ አፍሮ ታሪክየተመራመረ፤ ለሕዝብና ለሃገር አንድነት የቆመ፤ የተሟገተ፤ የዘመረ የአዲስ አበባና የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅናከያኔ ነው። ኢትዮጵያንና ታሪኳን ፤ፍቅርንና ሰላምን ሲያዜም ኖሯል። በመረዋ ድምጹ ኢትዮጵያን በፍቅር ይዞ ሊጓዛ የተነሳየልጅ አዋቂ፤ አስተማሪና ሰባኪም ነው። የመልካም ስነምግባሩናየኪነት ውጤቱ የሆነውን ‘ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ’ የተሰኘውን የሙዚቃ ውጤቶች ለህዝብ ለማቅረብ ለአያሌ ዓመታት ሲባዝን ኖሯል። ብዙ ጊዜ ሞክሮ ሳይሳካለት ቆይቷል።
የፍቅር ጉዞ መልዕክቱን ለሕዝብ እንዳያቀርብ ሲከለክሉ የቆዩ የኢሕአዴግና ሕወሃት ባለስልጣናት አንገላተውታል። ሕዝቡም ፍቀዱለት እያለ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሲጠይቅና ጫና ሲአደርግሃያ ዓመት በምጥ ኖሯል። ዛሬ ቴዲ ተከልክሎ የነበረው ተፈቅዶየፍቅር ጉዞ ኮንሰርቱንና የሙዚቃ ቅኝቱን ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን2012 ለሕዝብ አሳይቷል። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል እንዲሉት እግስትም ፍቅርን ወለደች። አዲስ አበባና ኢትዮጵያም እንኳን ደስያላችሁ። በኮንሰርቱ ኢትዮጵያዊነትና ሰባዊ ፍቅር ነግሰውአምሽተዋል።
የኢትዮጵያና የዓለም ማህበረሰብ ለዓመታት ሲአምጥ የኖረውንከባድ ምጥ በኮንሰርቱ ተገላግሏል። ምጡ በቀዶ ጥገና ሳይሆንበተፈትሮ ሕግ ፆታ የሌለው፤ በልብ ቅርጽና በቀይ አበባ የሚመሰለው ሁሉን የሚያስማማ ፍቅርና ኢትዮጵያዊነት የተባሉመንታ ልጆችን ወልደው ተገላግለዋል። መልካም ልደት።
በመጨረሻም 150, 000 ሕዝብ በመስቀል አደባባይ በፍቅርሲታደም ያለኮሽታ፤ ሕይውት ሳይጠፋ፤ ንብረት ሳይወድም የቴዲመርሃ ግብር በሰላም እንዲጠናቀቅ በማድረጋችሁ ለአዲስ አበባሕዝብና ወጣቶች አክብሮታችን የላቀ ነው። የፍቅርና የሰላምከተማ መሆኗን ስላስመሰከራችሁ በድጋሜ እንኳን ደስያላችሁ፤ ደስያለን። ቴዲም በሕዝብ መወደድና በፍቅር መጓዝ ያለውንጥቅም ስላሳየኸን እግዚአብሔር እደሜና ጤና ይስጥህ–ኑርልን።
የሁሉም ሙዚቃዎችህ ሱሰኛና የባህር ማዶ አድናቂህ…