የአዲስ አበባ ባቡሮች የኤሌክትሪክ ገመድ እየተዘረፉ ነው፤ ጉዞ ተስተጓጉሏል

የአዲስ አበባ ባቡሮች የኤሌክትሪክ ገመድ እየተዘረፉ ነው፤ ጉዞ ተስተጓጉሏል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ምሽት ላይ በሚፈጸም የሲግናል ኮሚኒኬሽን ኬብል እና የኤሌትሪክ ገመድ ስርቆት ምክንያት በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙ 35 ባቡሮች ላይ በምሽት በሚፈጸም የባቡር ኤሌትሪክ ገመድ እና የሲግናል ኮሚኒኬሽን ኬብል ስርቆት ምክንያት ከፍተኛ መስተጋጉል እያጋጠመ መሆኑን፤ በአገልግሎቱ የጥገና ማዕከል ዳይሬክተርና ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ታመነ ሽመልስ ተናግረዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም በሲ ኤም ሲ እና በሌሎች መስመሮች ከፍተኛ የትራንስፖርት ስምሪት መስተጓጎል ማጋጠሙ ተጠቁሟል። እየተፈፀመ የሚገኘውን ስርቆት ለመከላከል ለሚመለከታቸው አካላት ማመልከታቸውን አቶ ታመነ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በግማሽ ዓመቱ አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙት 35 ባቡሮች 72 ሚሊየን 730 ሺህ 606 ብር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY