ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን ትራፊክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በ835 ሚሊዮን ብር ወጪ እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስጀመሩ፡፡
ማዕከሉ የትራፊክ መረጃዎችን በማሰባሰብ የትራፊክ መብራቶች የቆይታ ጊዜን የትራፊክ ፍሰቱን መጠን የመቀያየርና ልዩ ልዩ የትራፊክ ፍሰት ማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወስዱ የማድረግ ተግባራትን ያከናውናል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አከለ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ እንደተናገሩት ጣቢያው ባለአራት ወለል ሲሆን የወንጀልና አደጋ መከላከል ቢሮዎች የመረጃ ማደራጃና ሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያሰችል ሆኖ እንደሚደራጅ ተናግረዋል፡፡
የትራፊክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሕንፃው ባለ አራት ወለል ሲሆን በ10 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ እንደሆነና ግንባታውም በ18 ወራት እንደ ሚጠናቀቅና ለግንባታው 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በጀት መያዙን ገልጸዋል፡፡