ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጉምሩክ ኮሚሽን የተያዙ ተሽከርካሪዎች በአንድ ወር ጊዜ ታርጋ እንዲቀይሩ ተወሰነ።
በ2008 ዓ.ም ያገለገሉ የዶልፊን ቫን ተሽከርካሪዎች በታርጋ ውዝግብ ምክንያት ኤክሳይዝ ታክስ ሳይከፋልባቸው ወደ አገር እንዲገቡ የተደረጉ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ያቀረቡት ቅሬታን መፈታቱን ጉምሩክ አስታወቀ፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ምንም እንኳን ባለንብረቶቹ የተወሰነውን ውሳኔ የተቀበሉት ቢሆንም ኮሚሽኑ በአንድ ወር ጊዜ ወስጥ ተሽከርካሪዎቹ ወደ ኮድ 3 ወይንም ኮድ 1 እንዲቀይሩ፤ ለእቃ ወይንም ለሰው ጭነት አገልግሎት እንዲያውሉ ጊዜ በመስጠት ለተፈጠረው ችግር መፍትኄ ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡
የተሰጠው እድል የመጨረሻ በመሆኑ ተመሳሳይ ድርጊቶች ፈፅመው ቢገኙ፣ ኮሚሽኑ ሳይከፈል የቀረበውን ኤክሳይዝ ታክስ የሚያስከፍል መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አስታውቋል፡፡