ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች ምዝገባ የጊዜ ገደብ አስቀመጠ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች ምዝገባ የጊዜ ገደብ አስቀመጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሀገር አቀፍና የክልል ፓርቲዎች እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 በሚቆይ የጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታቸውን አሟልተው እንዲመዘገቡ አሳሰበ፡፡

በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ምርጫ አዋጅ ቁጥር 162/2011 እና በዚሁ አዋጅ መሰረት በቦርዱ ሀገር አቀፍ እና የክልል ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን ግዴታ ለማስፈፀም በወጣው መመሪያ ቁጥር 03/2012 መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ግዴታቸውን በመወጣት እንዲመዘገቡ የጊዜ ገደብ አስቀምጧል፡፡

ቦርዱ እንዳሳወቀው እስከአሁን ድረስ ግዴታቸውን አሟልተው የተመዘገቡት ፓርቲዎች ቁጥራቸው አነስተኛ ነው ብሏል፡፡

LEAVE A REPLY