ኢትዮጵያ ውሳኔ ይሰጥበታል በተባለው የአሜሪካው የአባይ ግድብ ስብሰባ አትሳተፍም

ኢትዮጵያ ውሳኔ ይሰጥበታል በተባለው የአሜሪካው የአባይ ግድብ ስብሰባ አትሳተፍም

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበታል በተባለውና የአሜሪካ መንግስት ባሰናዳው የአባይ ግድብ ስብሰባ እንደምትገኝ ገልጻለች።

የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ሂደትና አፈጻጸም ዙሪያ ለበርካታ ወራት የሶስትዮሽ ውይይት ሲካሄድ ቆይቷል። ነገር ግን አሜሪካንና የአለም ባንክ ለታዛቢነት ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ድርድር እየተካረረ መምጣቱ ይታወሳል።

የአማሪካን  መንግስት ሁኔታውን ለመቋጨት ለፌብርዋሪ 27/2020 ግብጽ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ለመሰብሰብ በቀጠረችው መሰረት ነበር ጥሪውን ያስተላለፈችው።

በስብሰባው ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ የገለጸተ የኢትዮጵያ በአሜሪካን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍፁም አረጋ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፡ –

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመደረግ ላይ ያለው ውይይት ባለማጠናቀቁ ኢትዮጵያ የአሜሪካ የትሬዥሪ ዲፓርትመንት እ.ኤ.አ. ከፌብሩዋሪ 27-28/2020 በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በቀጠረው መድረክ ላይ መገኘት እንደማትችል አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን አሳልፎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት ስምምነት አትፈጽምም:: ሲሉም አምባሳደሩ በመልዕክታቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

LEAVE A REPLY