ህወሓት ከለቀቃቸው ከ2 በላይ እስረኞች የወልቃይትና የራያ ተወላጆች የሉበትም ተባለ

ህወሓት ከለቀቃቸው ከ2 በላይ እስረኞች የወልቃይትና የራያ ተወላጆች የሉበትም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ  መንግሥት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ይፋ አድርጓል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ተኪኡ ምትኩ የክልሉ መንግሥት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ነው የተናገሩት።

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ጥሩ ሥነ ምግባር ያሳዩና በጥፋታቸው የተፀፀቱ መሆናቸውን አመራሩ አስረድተዋል።

የይቅርታ ህጉን አሟልተው ለተገኙ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓልም ብለዋል። ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥም 46ቱ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

ትግራይን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ከሁለት ሺኅ በላይ የህግ ታራሚዎችን ለቀቅኹ ቢልም በትግራይ ሕዝብ ስም የሚነግደውን የወያኔን ሥርዓት አምርረው የተቃወሙ የአረና ፓርቲ አባላትና ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆችና ከመሬት ይዞታ ጋር የታሰሩ የወልቃይትና የራያ ተወላጅ ሆነው በግፍ ከታሰሩ በርካታ ንጹሃን እስረኞች መሀል አንድም ሰው አለመፍታቱን የኢትዮጵያ ነገ ታማኝ የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል::

LEAVE A REPLY