በህገ ወጥ ደላሎች ወደ ሱዳን ሊጓዙ የነበሩ 96 ሴቶች ጎንደር ተያዙ

በህገ ወጥ ደላሎች ወደ ሱዳን ሊጓዙ የነበሩ 96 ሴቶች ጎንደር ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ለመሻገር የሞከሩ 96 ሴቶች መያዛቸውን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።

ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡት ሴቶች ጎንደር ከተማ ባረፉበት ሆቴል ውስጥ ከኅብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ መያዛቸውን፥ የጎንደር ከተማ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የስልጠናና ግንዛቤ ማስጨበጥ ንዑስ ክፍል ሓላፊ ዋና ሳጅን ታደሰ አለምነህ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ሁሉም ሴቶች በፖሊስ ጣቢያው የሚገኙ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎችም የምግብ እና ሌሎች ድጋፎችን እያደረጉላቸው ይገኛልም ተብሏል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አንድ ወንድ እና ከስደተኞቹ ጋር የነበረች ሴት በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ እና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ክትትል እየተደረገ መሆኑም ተሰምቷል።

ህገ ወጥ ደላሎች በአዲስ አበባ በኩል የሚደረጉ ጉዞዎች ተከልክለዋል በሚል የስደት ተጓዞቹን ወደ ጎንደር በምሽት በመላክ ከ15 እስከ 20 ሺህ ብር እንዳስከፈሏቸውም መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

LEAVE A REPLY