ቀን፤ የካቲት 20, 2012
በአንፃሩ በሃብቷ ተምረው ስሟን ያጎደፉ፤ ሕልውናዋንየተፈታተኑ ከሃዲዎች መኖራቸውን ስናይ እናዝናለን። እነዚህንየመሰሉ ልጆቿ ሃገሪቱን አመድ አፋሽ አርገዋታል። ይህ የቅርብጊዜ ክስተት ብቻ ሳይሆን በሶስት ሽህ ዘመን ጉዞዋ ሁሉ ሲከሰትየኖር ለመሆኑ ታሪክ ይነግረናል።
ያአሁኑን ከጥንቱ ለየት የሚአደርገው ያለንበት ሃያ አንደኛውክፍለ ዘመን መሆኑ፤ ልጆቿ ዘመናዊ ትምህርት ያላቸው፤ ዓለምበቴክኖሎጂ ረቆ ህዋ ላይ የተንሳፈፈበት፤ ሃገራችን ሳተላይትወደ ጠረፍ የላከችበት ዘመን ላይ መሆኑን ስናይ ቁጭታችንይበረታል። ከታሪክና ከስህተታችን መማር አለመቻላችን ይበልጥያስቆጫል።
በነዚህ መካከል ጥሩ ሲሰሩና ሲሞገሱ የማይወድላቸው፤ ፀዱሲባል ታጥበው ጫቃ የሚሆኑ አንዳንድ ምሁራን እናገኛለን።ለዚህ ዶክተር መረራ ጉዲና ጥሩ ማሳያ ናቸው። ዶ/ር ጉዲናበወያኔ ዘመን ብዙ የተንገላቱ የፖለቲካ ምሁር ናቸው። መለስዜናዊን በአመክንዮ የሞገቱ፤ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ድርድርየማያውቁ እንደነበሩ እናውቃለን።
ላለፉት ሰላስ ዓመታት ባደረጉት የፖለቲካ ከርክርና እሰጥ አገባሕዝብ (ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖት፤ ፆታ፤ ጎሳና ጎጥ ሳይለይ) አመኔታየቸራቸው ምሁር ናቸው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግለትና ቅዝቃዜመለኪያ ‘ተርሞሜትር’ እስከመሆን ደርሰዋል። የፖለቲካውክርክር ሲጦዝ፤ አስታራቂ ሃሳብ ሲጠፋ፤ ነገሮች መስቀለኛመንገድ ላይ ሲደርሱ ዶክተር መረራ ምን አሉ ተብሏል። ለሐቅምስክርነት ማጣቀሻና ዋቢ እስከመሆን ደርሰው ነበር።በፓርላማ መለስን ያለፍርሃት ሞግተውታል። እንዲህ የሚሞግትባይኖር አምባገነኖች ካደረሱብን እርግጫ በባሰ እንረገጥ ነበር።
ዶክተር መረራ እንዳሉን መለስ ሲሻው ማሞካሸት ሲናደድማበሻቀጥን ያውቅበታል። ጥላቻው አይድረስባችሁናሲአሞካሽም ሆነ ሲአጥላላ ግብረገብነት የጎደለው ነበር:: በጸያፍ አንደበቱ አዛውንት፤ ካህን፤ ሸህ፤ ሽማግሌ፤ ምሁር፤ ወጣት፤ ሴት ወንድ ሳይለይ በእፅ የሰከሩ ሰዎች በሚናገሩትቋንቋ ሰውን ሲዘልፍ ቅር አይለውም። የዓይን ቀለምአላማረኝም ብሎ ሕዝብ የሚአፈናቅል፤ የዩንቨርሲቲፕሮፌሰሮችን የሚአባርር መሪ ይህን ባይል ነበር የሚገርመው።
በአንድ ቃለ ምልልስ መለስ እንዴት ይጠሩዎት ነበር ተብለውሲጠየቁ ዶክተር ጉዲና ፈገግታ፤ ቀልድና ፌዝ ተልይቷቸውስለማያውቅ በሳቅ ታጅበው የሰጡት መልስ ‘ሃሳቤንናአስተያየቴን ሲወዱት ዶክተር መረራ ይሉኛል፤ በሃሳቤሳይደሰቱ ደግሞ አቶ መራራ’ እያሉ ይጠሩኝ ነበር ብለዋል።
ከኦሮሙኛ ተናጋሪ ወንድሞቸ እንደተረዳሁት መረራ ማለትአስተዛዛኝ፤ ጉዲና ደግሞ እድገት ማለት እንደሆነገልጽውልኛል-ነን ሶቤ! መለስ ደስ ሲላቸው አስተዛዛኙ መረራሲከፋቸው ደግሞ ቆምጣጣው ወይም መራራው (bitter) እያሉበገደምዳሜ ይሰድቧቸው ነበር ማለት ነው። ዶክተሩም የዋዛስላልሆኑ በመልስ ምት አሁንስ መንጌን መስለው ታዩኝ ይሏቸውእንደነበር ሰምተናል። በዚህ ደረጃ ባለሥልጣን የሚፈታተኑ ቅንፖለቲከኛ ነበሩ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዶክተር መረራ በሚናገሯቸውናበሚሰሯቸው ሁሉ መራራነታቸውን እየመሰከሩ ሲአልቅ አያምርእየሆኑ መጥተዋል። ተደብቆ የነበረው ገጽታቸው አደባባይእየወጣ ግራ ተጋብተው ግራ አጋብተውናል። ከጽንፈኛ እናከፀረ–ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር ህብረት ፈጥረው ተገቢ ያልሆነነገር በመናገር ሕዝብን እያስቀየሙ ይገኛሉ።
በተለይ የጃዋር ዜግነትን በተመለከተ እርስበርሱ የሚጣረስአምክንዮቢስ ንግግራቸውን የሰማው ሕዝብ መረራ ምንነካው እስከማለት ደርሷል። ጃዋር አሜሪካዊ ዜጋ መሆኑንእያወቁ የቀበሌ መታወቂያ ሰጠው በራሳቸው ስልጣንኢትዮጵያዊ ዜግነት ሲአጎናጽፍ አገር ጉድ አለ። አሰራሩ በሕግየሚአስጠይቃቸው መሆኑንም ዘነጉት። ጃዋር ኢትዮጵያዊመልክ ስላለው ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ የማይመለስበት ምክንያትእንደማይገባቸው ሲናገሩ አገር ተገረመ።
የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል ካልህነ በቀር መረራ ምርጫቦርድ፤ ብርቱካን እና የዜግነት ሁነት ኤጀንሲ ከሕግ ውጪመስራት እንዳለባቸው ግፊት እያረጉ መሆኑን ሳያውቁትቀርተው አይደለም። በቅርቡ ከዶክተር ዓብይ ፊት ቀረበውስለጆርጆ ዖርዌል (George Orwell-84) ሁሉም እንስሶች እኩልናቸው ግን ትቂት እንስሶች የበለጠ እኩል ናቸው ብለው ንግግርሲአሳምሩ ሰምተናል። ዶክተር መረራ በዜግነት አመላለሱ ሂደትየጆርጅ ዖርዌል ሕግ እንዲፈጸም እየጠየቁ መሆኑን አውቀውትይሆን። ለምን የሕግ የበላይነት ይከበር እያሉ ሕዝባዊ ሰልፍእንደሚጠሩ ግልጽ አይደለም።
ቀስበቀስ ከዶክተር መረራ ጉዲናነት ወደ ዶክተር መራራጉዲናነት መሸጋገር ጀምረዋል። ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ምሁር ሲዘቅት ይመራልና አድብ ገዝተው ወላጆቻቸውወዳወጡላቸው አስተዛዛኝ እድገት/ብልጽግና ስማቸውቢመለሱ ለስብዕናቸውም ሆነ ለቀሪው ሕይወታቸውየሚበጃል። ካልሆነ እንደ ስልሳ ስድስቱ ጓዶቻቸው ወጣ ወጣእንደ ሸንበቆ ተንከባለለ እንደሙቀጫ ብለን ጫንጮ እናሸፍታቸው።