ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ያስገነባውን የስነ አዕምሮ፣ ድንገተኛ ህክምና እና የእናቶችና የሕጻናት ጤና አገልግሎት መስጫ ህንፃ አስመረቀ።
ህንፃው የተገነባው ሙሉ በሙሉ ሃይኒከን አፍሪካ ፋውንዴሽን ባደረገው ድጋፍ ነው መባሉንም ሰምተናል። በምረቃ ስነ ሥነርዓቱ ላይ የሃይኒከን አፍሪካ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎችን ጨምሮ የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዳኦ ፈጆ፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች እና የሆስፒታሉ ሠራተኞች ተገኝተዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዳኦ ፈጆ በጊዜ ሂደት የህክምና ሁኔታው እየተሻሻለ እና የባለሙያ እጥረት እየተቀረፈ ቢመጣም የመሠረተ ልማት ችግር ግን አሁንም አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን ጠቁመው ፤ ሆስፒታሉ በቀን በተመላላሽ ህክምና ብቻ ለ580 ያህል የአዕምሮ ህሙማን አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱንም ገልጸዋል።
የተገነባው አዲስ ህንፃ ለተለያዩ የስነ አዕምሮ ድንገተኛ ህክምና እና ለእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት መስጫ የሚውሉ 23 ክፍሎች እንዳሉት ታውቋል።