ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካ የዓለም ዐቀፍ ልማት ኤጀንሲ ዩኤስ ኤድ ኢትዮጵያ ለምታካሂዳቸው ምርጫዎች የሚውል ከ 30 ነጥብ አራት ሚሊዮን ዶላር ባለይ ድጋፍ ማድረጉ ታወቀ፡፡
የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እና የዩኤስ ኤድ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ዛሬ የካቲት 20/2012 ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል።
የአሜሪካን መንግሥት ያደረገው ከፍተኛ ድጋፍ ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ተዓማኒ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ግልፅነት የሰፈነበት እንዲሆን የሚያደርጉ ሥራዎች ለማከናወን እንደሚውል ተነግሯል፡፡