በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የ55 ዓመት ዜጋ መሞቱ ተረጋገጠ

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ የ55 ዓመት ዜጋ መሞቱ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የመጀመሪያውበአሜሪካ በዋሽንግተን ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ አንድ ሰው መሞቱ ይፋ ተደረገ። ባለሥልጣናት ሟቹ  ግለሰብ በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝና ሌሎች በሽታዎች ያሉበት ሰው ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ሌሎች የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ሊኖሯት እንደሚችሉ ሲሉ  የአገሪቱ ባለሥልጣናት ደግሞ “ለቫይረሱ ከማንም በላይ ዝግጁ ነን” ሲሉ ለዜጎቻቸው ደሕንነት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

በተመሳሳይ ለኑሮ ተመራጭ ናት የምትባለው አውረስትራሊያም ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰው እምደሞተባት ገልጻለች። ግለሰቡ በዳይመንድ ፕሪንሰስ መርከብ ውስጥ የነበረ የ78 ዓመት አዛውንት መሆኑም ታውቋል።

እስካሁን በ57 አገራት ከ85 ሺህ በላይ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች መኖራቸው ተረጋግጧል። 3 ሺኅ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል ያለው የዓለም ጤና ድርጅት ብዙዎች የቫይረሱ ተጠቂዎችና ሟቾች ቫይረሱ ከመነጨባት ቻይና እንደሆነም አስታውቋል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሟቹ የቫይረሱ ስጋት ወደ አለበት አካባቢ እንዳልተጓዘ መግለፃቸውን ተከትሎ የዋሽንግተን አገረ-ገዥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ካሊፎርኒያ፣ ኦሬጎን እና ዋሽንግተን ግዛቶች ውስጥ የቫይረሱ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ያልሄዱ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኝ አንድ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ክበብ ሁለት ሰዎች የቫይረሱን ምልክት አሳይተው ወደ ጤና ጣብያ ተወስደዋል። ሌሎች በርካታ የክበቡ አባላት ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። የዓለም ጤና ድርጅት አሜሪካ ውስጥ እስካሁን 62 ሰዎች የቫይረሱ ተጠቂዎች መኖራቸው ተረጋግጧል ብሏል። አንድ አሜሪካዊ በቅርቡ ቫይረሱ በመነጨባት ዉሃን መሞቱ ይታወሳል።

ትራምፕ፤ ምንም እንኳ ቫይረሱ አገራቸው ቢገባም የሚያስደነግጥ ነገር የለም የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ በበኩላቸው ኢራን ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እግድ እንደሚቀጥልና ባለፉት 14 ቀናት ኢራንን የጎበኘ ማንኛውም የውጭ ዜጋ ወደ አገራቸው እንደማይገባ አሳስበዋል። ኢራን ከቻይና ውጭ ብዙ ሰው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞተባት አገር ሆናለች።

LEAVE A REPLY