ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያና የአገር ሽማግሌው አቶ ውብሸት ወርቃለማው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ወብሸት ወርቃለማሁ ባደረባቸው ህመም በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ትናንት እኩለ ሌሊት ነው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው።
በኢትዮጵያ የማስታወቂያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የነበሩት አቶ ውብሸት “አንበሳ” የተሰኘ የማስታወቂያ ድርጅት በመክፈት ለሙያው ዕድገት ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ውብሸት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል በመሆን አገራቸውን በመወከል የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነትን በማሻሻሉ እና በአገር ሽማግሌነት ለሕዝብና ለአገር ፋይዳ ያላቸው በርካታ ሥራዎችን በብቃት የተወጡ መሆናቸው ይታወቃል።