ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዲሪ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት የተለያዮ የመንግሥት ሹመቶችን ሰጥተዋል:: በሹመቱ በለውጡ ማግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሆነው የተሾሙት ብርሃኑ ጸጋዬ ከሓላፊነታቸው ተነስተው በአምባሰደርነት ተሹመዋል:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገዢም ተመሳሳይ ሹመት ተሰጥቷቸዋል::
በቅርቡ በከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት የሚጠረጠሩ እና የንጹሐን ዜጎችን ደም ያፈሰሱ ወንጀለኞችን ከፖለቲካ እና ከህሊና እስረኞች ጋር በመለቀቃቸው የሚወቅሱት ብርሃኑ ጸጋዬ ከሓላፊነት መነሳታቸው ተገቢ መሆኑን በርካታ ኢትዮጵያውያን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየገለጹ ናቸው።
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘው የሰጡት ሹመት ሙሉ ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
1. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
2. ወ/ሮ የአለም ፀጋዬ
3. ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ
4. አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ
5. አቶ ባጫ ጊኒ
6. አቶ ይበልጣል አዕምሮ
7. አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ
8. አቶ ነብያት ጌታቸው
9. አቶ ተፈሪ መለስ ተሹመዋል፡፡
እንዲሁም
1. አቶ አድጐ አምሳያ
2. አቶ ጀማል በከር
3. አቶ አብዱ ያሲን
4. አቶ ለገሠ ገረመው
5. ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማርያም እና
6. አቶ ሽብሩ ማሞ በአምባሳደርነት ማዕረግ ሹመት አግኝተዋል፡፡