ጣሊያን 1ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመች

ጣሊያን 1ቢሊዮን ብር ድጋፍ ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ1 ቢሊየን 40 ሚሊየን ብር የድጋፍ እና የብድር ስምምነት  በአደዋ ድል ማግስት መፈራረማቸው ተነገረ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አርቱሮ ሉዚ የተፈራረሙ መሆናቸው ታውቋል።

ከተፈጸመው ስምምነት ውስጥ 456 ነጥብ 98 ሚሊየን ብሩ ድጋፍ ሲሆን ቀሪው 575 ነጥብ 72 ሚሊየን ብር ደግሞ ብድር መሆኑ ተገልጿል። ገንዘቡ ለሸገር ማስዋብ ፕሮግራም፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክልሎች ለጤና ትግበራ እና ለሌሎች መሠረተ ልማቶች የሚውል መሆኑ ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY