ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብልፅግና የተሰኘውን በቅርጽና በአሠራር መዋቅር ፈጽሞ ከኢሕአዴግ የማይለየውን ፓርቲ የመሠረቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀጣዮን አገራዊ ምርጫ በአዲሱ ፓርቲያቸው ለማሸነፍ በየክልሉ የሚያደርጉትን ቅስቀሳ አጠናክረው ቀጥለዋል::
የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ለሚደረገው ውይይት ወደ ስፍራው አቅንተዋል።
ከምርጫው አስቀድሞ በመላ አትዮጵያ ስለብልፅግና ራዕይ እየሰበኩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በከተማዋ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚወያዩ ሲሆን በስታዲየም ለተሰበሰቡ ነዋሪዎችም ንግግር እንደሚያደርጉም ከቅድመ መርሀ ግብሩ መረዳት ችለናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባለፉት ሳምንታት በወራቤ፤ ዱራሜና ሃላባ ቁሊቶ ከተሞች ጉብኝት በማድረግ ከኅብረተሰቡ ጋር ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡