የህወሓት አባል የነበሩት ወ/ሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ

የህወሓት አባል የነበሩት ወ/ሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነትና በተለያዩ የመንግሥት የሥራ ሓላፊነቶች ላይ ያገለገሉት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

ወይዘሮ ነፃነት ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ፣ የኢፌዴሪ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዲኤታ እና በሌሎች የሥራ ሓላፊነቶች ላይ ለህወሓት መራሹ  መንግሥት ለዓመታት መሥራታቸው ይታወቃል።

ወይዘሮ ነጻነት አፍቃሪ መለስ ዜናዊ መሆናቸው ለከፍተኛ የስልጣን    እንዲሰሩ ዕድል እንዲሰጣቸው  ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።  በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት /ኢጋድ/ ውስጥም የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር በመሆን ተሹመው ሰርተዋል።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወይዘሮ ነፃነት ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን በፍጥነት ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል:: የወይዘሮ ነፃነት የቀብር ሥነ ሥርዓት በመቐለ ከተማ የአርበኞች መቃብር ስፍራ የሚፈጸም መሆኑን ለኢትዮጵያ ነገ የደረሰው መረጃ ያሳያል።

LEAVE A REPLY