የለገሃሩ ሎጀስቲክ ሕንፃን ለማፍረስ ሰባት ወራት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም

የለገሃሩ ሎጀስቲክ ሕንፃን ለማፍረስ ሰባት ወራት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሆኖ ለ21 ዓመታት ያገለገለው ህንፃ ለለገሃር የተቀናጀ ልማት የቤቶች ግንባታ ታስቦ እንዲፈርስ ተወስኖ ሙከራ ቢደረግበትም እስካሁን ድረስ ህንፃውን ሙሉ ለሙሉ ማፍረስ እንዳልተቻለ ታወቀ።

ባለ ስምንት ፎቁ ህንፃ ፍፁም ጠንካራ በመሆኑ ለሰባት ወራት ያህል የተደረገበት የማፍረስ ሙከራ ሊሳካ አልቻለም:: ህንፃው ለ50 ዓመታት  አገልግሎት ታስቦ ከ21 ዓመት በፊት የተገነባ ሲሆን ለግንባታው ባለ 32 ቁጥር እና ባለ 16  ቁጥር  ፌሬዎች ሥራ ላይ በመዋላቸው የማፈረስ ሥራውን የማይቻል እንዳደረገው የማፍረስ ሥራውን አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው በጥቃቅንና አነስተኛ  የተደራጁ ወጣቶች ገልጸዋል::

እነዚህ በኮንስትራክሽን ሥራ የተሰማሩት ወጣቶች ሕንፃውን የማፍረስ ሥራውን ማገባደድ  ባለመቻላቸው የቀን ሠራተኞቻቸውን አሰናብተው አዳዲስ አማራጮችን በመፈለግ ላይ መሆናቸው ታውቋል:: ከቀድሞው የኢትዮጵያ  ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ አገልግሎት ድርጅት ዋና መሥሪያ አጠገብ የሚገኙ ህንፃዎች በቀላሉ ፈርሰው የተጠናቀቁ መሆናቸውን ያመላከተው ዜና ህንፃዎቹ ባለ አራት እና አምስት ወለል ያላቸው ከ35 እስከ 40 ዓመት ያስቆጠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል::

LEAVE A REPLY