ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ በአዲስ አበባ በአንድ ጃፓናዊ አማካይነት ከስምንት ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ መረጃው ቅድሞ የደረሳቸው በርካታ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ማረጋገጫ ከመስጠቱ ከሁለት ቀናት በፊት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በጉዳዮ ላይ መረጃ ያሰባሰበው የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን አረጋግጧል።
በተለይም ከማክሰኞ ከሰዓት በኋላ አንዳንድ ኤንባሲዎች ከውጭ ከሚመጡ ባለ ጉዳዮች ጋር ያላቸውን ቀጠሮ መሰረዛቸውና ይህ አሠራር በማግስቱ ረቡዕ መቀጠሉ ታውቋል።
በአዲስ አበባ ያሉ በርከት የተለያዩ ኤምባሲዎች የኮንሱላር አገልግሎቶቻቸውን በተለይ ከዛሬ መጋቢት 4/2012 ጀምሮ ያለማቋረጥ የጀመሩ ሲሆን፤ ከተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮም አንዳንድ ኤምባሲዎች ስብሰባዎቻቸውን መሰረዛቸውን ዘጋቢያችን አስታውቋል፡፡
የአውሮፓ አገር ኤንባሲዎች አገልግሎቱን መስጠት ካቆሙት ዋነኞቹ ሲሆኑ የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ የሆኑት ዮርዳኖስ አለባቸው በኢትዮጵያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው ያለመገኘቱን ገልፀው ኤንባሲዎቹ ለምን አገልግሎት እንዳቆሙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የተናገሩ ቢሆንም መንግሥት ዛሬ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አማካይነት አንድ ጃፓናዊ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት መሆኑን ይፋ አድርጓል።