አጠራጣሪ ለሆነው ቀጣዮ ምርጫ ቦርዱ የምርጫ ክልሎችን ይፋ አደረገ

አጠራጣሪ ለሆነው ቀጣዮ ምርጫ ቦርዱ የምርጫ ክልሎችን ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀጣዮ አገራዊ የምርጫ ክልሎችን ይፋ ማድረጉ ታወቀ:: የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች የተካፈሉበት፥ የምርጫ ክልሎች ይፋ የሚደረጉበት የውይይት መድረክ ዛሬተካሄዷል።

በመድረኩ የምርጫ ክልል ምነንነትና አከላለል፣ እንዲሁም የከዚህ በፊት አከላለልና ህጋዊ ማዕቀፍን አስመልክቶ ማብራሪያ በምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተሰጥቷል።

በውይይት መድረኩ ላይ ለመጭው ጠቅላላ ምርጫ የተዘጋጀው የምርጫ ክልሎች ካርታም ይፋ ሆኗል። በዚህ መሰረት 547 የምርጫ ክልሎች ይፋ መደረጋቸውን ታዝበናል።

ይፋ በሆነው ካርታ መሰረት ትግራይ 38፣ አፋር 8፣ አማራ 138፣ ኦሮሚያ 178፣ ሶማሌ 23፣ ቤኒሻንጉል 9፣ ደቡብ 123፣ ጋምቤላ 3፣ ሀረሪ 2፣ ድሬዳዋ 2 እንዲሁም አዲስ አበባ 23 ለፌደራል ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ይኖራቸዋል ተብሏል። አሁን ያሉት የምርጫ ክልሎች በ1976 ዓ.ም በደርግ ዘመን የተካሄደውን የህዝብና ቤት ቆጠራ መሰረት በማድረግ በ1985 ዓ.ም መካለላቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY