በትግራይ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መረጃ መቀባበያ ነፃ የስልክ መስመር ይፋ ተደረገ

በትግራይ ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መረጃ መቀባበያ ነፃ የስልክ መስመር ይፋ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በትግራይ ክልል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ተደረገ።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ሀጎስ ጎደፋይ በትዊተር ገጻቸው እንደጻፉት ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ያሉ መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ነጻ የስልክ መስመር በትግራይ ክልል ከዛሬ መጋቢት 5 ቀን ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

በዚህ መሠረት ኅብረተሰቡ 62 44 ነጻ የስልክ መስመርን ከዛሬ ጀምሮ በመጠቀም ቫይረሱን በሚመለከት መረጃዎችን ማድረስ ይችላል ሲሉ አስታውቀዋል።

በክልሉ ቫይረሱን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑንም ሓላፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ በግልጽ አስቀምጠዋል::

LEAVE A REPLY