ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለም ላይ ገዳይነቱ በፍጥነት እየተዛመተ የመጣው በኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዙት ሰዎች ቁጥር አራት መድረሱ ተሰማ::
መንግሥት አርብ ዕለት በጤና ጥበቃ ሚኒስትር አማካይነት ይፋ ባደረገው መግለጫ አንድ ጃፓናዊ በአዲስ አበባ በቫይረሱ መያዙን መረጋገጡንና ከግለሰቡ ጋር ንክኪ ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሃያ አምስት ሰዎች በጥርጣሬ ተይዘው በጥብቅ ክትትል ውስጥ እንዲቆዮ መደረጉን ገልጾ ነበር::
የኢትይጵያ ነገ ታማኝ ምንጭች ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ባደረሱን ዜና መሠረት አዲስ አበባ ላይ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ሠዎች ቁጥር በዛሬው ዕለት አራት መድረሱን አረጋግጠውልናል::
ይፋ ባልሆነው ትክክለኛ መረጃ መሠረት ሁለት ጃፓናውያንና አንድ ኢትዮጵያዊ አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መህናቸው ታውቋል:: ሥስቱም ግለሰቦች መጀመሪያ በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠው ጃፓናዊ ቀጥተኛ የሥራ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆኑ ሁለቱ ጃፓናውያን የ40 እና የ70 ዓመት እድሜ ኢትዮጵያዊው ደግሞ የ42 ዓመት ሰው መሆኑን የኢትይጵያ ነገ ምንጭች ገልጸዋል::
አሁን ላይ በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው በሚል ተጠርጥረው በማቆያ ያሉት ሠዎች ቁጥር 160 መድረሱን ያገኘነው መረጃ ያሣያል::