የአውሮፓ አገራት በኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ የሞት መጠን እያስመዘገቡ ነው

የአውሮፓ አገራት በኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ የሞት መጠን እያስመዘገቡ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሦስት የአውሮፓ ኅብረት አገራት እስከ ዛሬ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በቀን ከተመዘገበባቸው የሞት መጠን አንጻር ትናንት ከፍተኛ የተባለውን የሞት መጠን አስመዘገቡ።

ጣሊያን በትናንትናው ዕለት 368 ስታጣ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 809  ከፍ ። ስፔን 97 ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 288 ደርሷል። በፈረንሳይም በትናንትናው ዕለት 29 ሰዎች ሲሞቱ በአጠቃላይ 120 ዜጎቿን በኮሮናቫይረስ ተነጥቃለች። የዩናይትድ ኪንግደምም ትናንት ብቻ 14 ሰዎች የሞቱባት ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ወደ 35 አድጓል።

በአውሮፓ መንግሥታት መመሪያዎችን በማጠናከርና የድንበር ቁጥጥሮችን በመጨመር ላይ ናቸው። ኦስትሪያ ከአምስት ሰው በላይ መሰባሰብ የተከለከለ መሆኑን  በይፋ አውጃለች። በብዙ የኅብረቱ አገራትም ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ኮሮናቫይረስ መነሻውን ቻይና ቢያደርግም አሁን ባለው ሁኔታ ግን ወረርሽኙ ዋነኛ ማዕከሉ አውሮፓ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል::

ስዊትዘርላንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 800 ሰዎች በበሽታው እንደተጠቁባት ታውቋል። አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂ ዜጎቿ ቁጥር 2 ሺህ 2 መቶ የደረሰ ሲሆን፣ የ14  ሰው ሞት ደግሞ ተመዝግቧል። በከፍተኛ ደረጃ የተጠቃችው ጣሊያንም በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 25 ሺህ ከፍ ብሏል።

ፈረንሳይ ወደ 7 ሺ 8 መቶ የሚጠጉ ህሙማን አሏት።  ስፔንም ወደ 5 ሺ 4 መቶ ሰዎችን መዝግባለች። የስፔን መንግሥት ዜጎች ሸቀጦችን ለመግዛት ወይም ለሥራ ካልሆነ ከቤት እንዳይወጡ አዟል። ፈረንሳይም ካፍቴሪያ፣ ሬስቶራንት፣ ሲኒማና በርካታ ሱቆችን ቆላልፋለች። የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌዬን ወረርሽኙን ተከትሎ ኅብረቱ የመከላከያ መሳሪያዎችንና መመርመሪያዎችን ማምረቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY