ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይመሰገንም! || ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይመሰገንም! || ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

የራስህ ሕዝብ በሞትና በሕይወት መሀል ሆኖእየተጨነቀ ባለበት ሰዓት አንድ ኩንታል 4000 ብር ሲገባሦስት በሦስት የሆነች አንዲት ጭርንቁስ ክፍል በወር ከ2000 ብር የበለጠ ስትከራይኑሮ እንደመንኮራኩር በየቀኑ ሲወነጨፍ ባለሁለትሽህና ከዚያም በታች የሚያገኙ የወር ደሞዝተኞች እንዴት ራሉ ቅንጣት የማያስብ መሪና መንግ ያለን ብቸኛ ሕዝብ እኛ ነን፡፡ በኮሮናቫይረስ ተጨንቀን ተጠበን የምገባበትን አጥ ሳለገብጋባ ነጋዴዎች አንዲት ሎሚ ብር 10 እና 15 እንዲሁም አንድ ኪሎ ነጭ ሽንኩርት 200 እና 250 ብር ሲሸ ዝም የሚል መንግሥት ማንን እየመራእን ደሆነ መረዳት አይቻልም (እርግጥ ነው አንዳንድ አካባቢዎች ይህን ችግር ለመቅረፍ ውሱን እንቅስቃሴዎች እንደሚደረጉ ይሰማልና ለነዚያ ዓይነቶቹ የሥራ ኃላፊዎች የሥምሪት አባላት ምሥጋናየን ማቅረብ እወዳለሁ)፡፡ ሁሉም እንደፈለገው ሆኖ ኳስ አበደች የመሰለ የጨረባ ተዝካር በኢትዮጵያ ገን ይታያል፡፡ በኪነ አለን እንጂ መንግሥት መኖሩ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ በደምባራ ፈረስ ቃጭል ተጨምሮ፡፡ በቡሃ ላይቆረቆር፡፡ ዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍሌላም ካለህ ጨምርበት፡፡ እኛም እንደዚህ ሆነናል፡፡

መንግሥቱ ጨካኝ እንጂ ኢትዮያዊጨካኝ ነበር፡፡ መንግ ዐረመኔ እንጂዐረመኔነቱ በዘርና በጎሣበሃይማኖትና በጎጥ መደቦች ያልተከፋፈለ ለሁሉም ነበር፡፡ አሁን ያለን ዘረኛ መንግሥት ግን ዕድሜ ለሕወሓትና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ለአንዱ የእንጀራ ልጅ ለሌላው የሥጋ ልጅ እየሆነ ሀገርና ሕዝ በመፍረስ አደጋ ውስጥ ናቸው፡፡ግን አንፈርስም!

መንጌ ገብጋባ በርበ ነጋዴዎች ላይ የወሰደውን የማያዳግም እርምጃ እናስታውሳ፡፡ አካሄዱ ህገ ወጥና ጭካኔ የተሞላበት ቢሆንም ውጤቱ ግን ለሕዝብ አልጠቀመም ማለት አንችልምፈረንጅ እንዲህ ይላል – Little temper settles the dust.  ሌላም ላክልልህ –  Even the nicest people have their limits. አንዳንዴ ክፉ መሆን ባትፈልገውም እንኳን መልካ ነው፡፡ ስልሳ ሰው የጫነ አውቶቡስ አንድሰው ለማዳን ብሎ ስልሳ ሰው ገደል ሊከት አይገባውም፡፡ በተመሳሳይም ጥቂት ጅብ ነጋዴዎች ይከፋቸዋ ተብ ሰፊ ሕዝብ በቁሙ እንጦርጦስ ሊገባ አይገባምና አንዳንዴ እያመመንም ቢሆን ጨከን እርምጃዎችን መውሰድ ሀገርንና ሕዝብን ከተጨማሪ ጉዳት ከማዳናቸው በላይ አስተማሪነታቸው የጎ ነው፡፡ ችግሩ ግን ሕግ አስከባሪተብዬውም በራሱ ወይ በቤተሰቡ ስም በንግዱ ዘርፍ ከገባና የሌቦች ተባባሪ ሆኖ ከተገኘ ነው፡፡ ያ ዓይነቱ ጉዞ ተያይዞ ጥፋት ነው፡፡ ሕግ አስከባሪ ከሌቦች ጋር በጥቅም ከተሻረከና ሙስና ሀገርን ካጥለቀለቀ የሀገርና የሕዝብ ኅልውና ልክ እንደኛ እንዳሁኑ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡ አሁን እኮ ሰው ገድለህ ብታመልጥ አንደኛ የሚከተልህ የለምሁለተኛ የሚከተልህ ቢኖር እንኳ የሙስና ድርሻውን ካንተወስዶ ፋይልህን መቼም እንዳይገኝ አድርጎ የሚቀብርልህ ኅሊናቢስ ሙሰኛ ነው፡፡ ሦስተኛ ወደየትም አቤት ብትል የሚሰማህ የለም (ሲጀመር አቤት መባያ ራሱ የለም)፡፡ ያለንበት ሁኔታ እኮ እኮያስጨንቃል ጎበዝ!

ጃዋር መሀመድ የመሰለ ዐረባዊ ኮሮኖና ቫይረስ እንደፈለገው ሲፈነጭ ማየትበቀለ ገርባን የመሰለኢቦላ ቫይረስ እንዳሻው ትዳር ሲያርስ መታዘብሕዝቅያስ ፀጋየ አራንሳን የመሰሉ ኢትዮ-ግብፃውያን ኤችአይቪዎች እንዳሻ ሕዝብን ሲያጋጩ ማየት ለእውነተኛ ኢትዮያውያን ትልቅ የኅ ቁስል ነው፡፡ ወቅቱ ነው ብለን ፍርዱን ለጊዜና ለፈጣ ብንተውም የቁስ ጥዝጠዛ ግን ዕረፍት ነሣን፡፡ ስለሆነም ክፉምቢሆን ፈን መናፈቅ ልናልጠው ያልቻልነው የወቅቱ ፍርጃ ሆነብን፡፡

ኢትዮጵያችን በሰብአዊና ተፈጥሯዊ የኮሮናቫይረሶች ተቀፍድዳ እዬዬ እያለች ነው፡፡ ፈጣሪበአፋጣኝ ይድረስላት፡፡ እንዳንዳች ነገር የሚከረፋውና የሚጠነባው ዘረኝነት ላይ ይህ ቫይረስ ተጨምሮ ሀገራችን ልትገልጽ የማት ቅርጸ ቢስ ሆናለች፡፡

ለማንኛውም መንጌ ሆይ ወዴት ነህ! በሃሳብ ደረጃም ቢሆን የበደልኩህን ይቅር በለኝ፡፡ ካንተ የባሱ የእፉኝት ልጆች መጥተው ራችንን እያበሉን መሆናቸውን ሳትከታተል አትቀርም፡፡ አንተ አሁን አርጅተሃል፡፡ ሥልጣን ቢሰጥህ እንኳ እንደዚያ እንደዱሮ በመስቀል አደባባይ እየተገማሸርክ በቀይ ቀለም የተሞላ ጠርሙስም ከግድግዳ ጋር እያጋጨህ እንደማትገዛን ግልጽ  ነው፡፡ ጊዜ እንዲህ ነው፡፡

ህን ጊዜ ባለውልነት ያልተረዱ ጎረምሦች ቤተመንግሥትን በዘ ወር-ተረኝ ተቆጥረው ፍዳንን እያሳዩን ነውና ፈጣሪ ሆይ ቶሎ ድረስልን፡፡ አጋንንታዊነ በቤተ መንግ ብቻ ሳይወሰን ቤተ አምልኮቶችንም በግላጭ ተቆጥሮ ከሃይማትም፣ ከሞራል ዕሤቶችም ከባህልም ከዕውቀት አምባምበሁሉም የሰውነት መለኪያ ሚዛኖች ስንለካ ወርደንና ቀለን  የለየለት እንስሳ ሆነናልና አምላክ ሆይ እንደገና ሥራን፡፡ እንደጠፋን እንዳንቀር ጀርባህን እንዳዞርክብን አትቅር፡፡

በነገራችን ላይ ከከብትም እንዳነስን መጠቆሜ ስህተት መሆኑ ይሰማኛል፡፡ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት እንስሳት ከኛ ይበልጣሉና፡፡ አንድ እንስሳ ከጠገበና ካልደረሱበት ማንንም አይተናኮልምአይነካምምእንስሳ ከተፈሯዊ ተግባሩ አያፈነግጥም፡፡ የወንድ እርግብ ሴት እርግብ ናትሊያውም አንድ ለአንድ በሚለው ሕግ ተመርተው፡፡ አንዲት ጉሬዛየምታገባው መሰሏ ወንድ ጉሬዛ ነው፡፡ አውሮፓውያን ከእንስሳት ጋር እንዲጋቡ ጋቸውን ማሻሻላቸውን እየሰማን አይደል ሰሞኑን? እኛ ሰዎች ስንባል እንግዲህ ተሰጠን አንጎል በከንቱ በማዋል ከሰው ተራ የሚያወጡ ተግባራትን እየፈጸምን ከራሳችን ኅሊና ከተፈጥሮ ከእግዜሩም ተለያይተናል፡፡ መጥኔ ለሰ ልጅ! ግን ግን ለዚህም ሁሉ ይከፈለዋልክፍያውም ጀምሯል፡፡ በቅርቡ ደግሞ ዓለማችን ትታደስና ሦሥት ዐይናማዎች በጉጉት የሚጠብቁት ወርቃማው ዘመን ይብታል፡፡ መንገድ ጠረጋው ነው ያለንበት፡፡ …

LEAVE A REPLY