ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሃገራት የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከየትኛውም ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ተጥሎባቸዋልም ብለዋል።
በዚህ ቆይታቸውም ሙሉ በሙሉ ወጪያቸውን ራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናል ሲሉም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም በማረሚያ ቤቶች፣ ቫይረሱ ከገባ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጠር በመሆኑ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑንም ገልጸዋል።
የእምነት ተቋማት እንደየአምልኳቸው ሁኔታ ለቫይረሱ ስርጭት ምቹ ሊሆኑ ስለሚችሉ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲያሳልፉም ከስምምነት መደረሱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ያደረጉት።