የዶ/ር ካትሊን የቀብር ስነስርአት በመጪው ሰኞ እንደሚፈፀም የፕ/ንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጽ/ቤት አስታወቀ

የዶ/ር ካትሊን የቀብር ስነስርአት በመጪው ሰኞ እንደሚፈፀም የፕ/ንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጽ/ቤት አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዶ/ር ካትሊን የቀብር ስነስርአት በመጪው ሰኞ እንደሚፈፀም የፕ/ንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጽ/ቤት አስታወቀ

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለዶክተር ካትሪን ሀምሊን በመኖሪያ ቤታቸው በመገኘት ስንብት አደረጉ። የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን ድንጋጌዎች በመተግበር፥ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት ዶክተር ካትሪን ሀምሊን መኖሪያ ቤት በመገኘት ስንብት አድርገዋል።

ለዶክተር ሀምሊን ልጅ የተሰማቸውን ሀዘን ሲገልጹምዶክተር ሀምሊን ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ከሚዳርገው የፌስቱላ ችግር ከ60 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን የታደጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ለዓመታት ያስተማሯቸውና ያሰለጠኗቸው በርካታ ባለሙያዎች ዶክተር ሀምሊን ሥራውን በጀመሩበትና በመሠረቱት ብቸኛው የፌስቱላ ሆስፒታል የእርሳቸውን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እርግጠኛ ነኝ  ሲሉ ፕሬዝዳንቷ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። የዶክተር ካትሪን ሃምሊን የቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ሰኞ ይፈጸማል መባሉን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ይፋ አድርጓል።

 

LEAVE A REPLY