ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከንግድ ጋር በተያያዘ መግለጫ የሰጡት የንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ መሀመድ በከተማዋ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር የከተማ አስተዳደሩ ግብረ ሃይል አቋቁሞ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የምርት እጥረት ከተከሰተም የከተማ አስተዳደሩ ከአርሶ አደሮች ምርቶችን በመረከብ ለተጠቃሚው በቀጥታ እንደሚያቀርብ አቶ አብዱልፈታ ጨምሮ ገልጸዋል፡፡
የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ ተመርተው የቀረቡት 200 ሺህ ሊትር ሳኒታይዘሮች በከነማ የመድሃኒት መደብር ፣ በሸማቾችና በሌሎች መንገዶች ለነዋሪው እየተከፋፈለ ይገኛል ብለዋል፡፡
ተጨማሪ ሳኒታይዘር በመመረት ላይ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ለከነማ ፋርማሲዎች የሚከፋፈል ይሆናል ብለዋል።
ከትራንስፖርት ስርአቱ ጋር በተያያዘ መግለጫ የሰጡት የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ስጦታው አከለም መጨናነቅን ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ በርካታ አማራጮችን ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ተጨማሪ አውቶቢሶችን ወደ ስራ በማስገባት ፣ የመንግስት መኪኖች ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ እየደረገ ይገኛል።
ታክሲዎች ከተፈቀደው መጠን በላይ እንዳይጭኑ ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን በቀጣይም ህጉን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱ የሚቀጥል ይሆናል።
እንዲሁም ሰልፍ ባለባቸው ቦታዎች ህብረተሰቡ ርቀቱን ጠብቆ እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርዋል፡፡
የታክሲ ሹፌሮች ፣ ረዳቶችና በየአከባቢው ያሉ ተራ አስከባሪዎች ህብረተሰቡ በቂ ርቀት ጠብቆ እንዲሠለፍ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ ማቅረ