የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች ከነገ ጀምሮ ሥራቸውን ከቤት እንዲያከናውኑ ተወሰነ

የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች ከነገ ጀምሮ ሥራቸውን ከቤት እንዲያከናውኑ ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት እንዳስታወቀው የሚንስትሮች ምክርቤት ዛሬ 17ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ካካሄደ በኋላ ውሳኔዎችንአስተላልፏል።

በዚህም የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች ከነገ መጋቢት 16 ጀምሮተጨማሪ ውሳኔ እስኪተላለፍ ድረስ ሥራቸውን ከቤት ሆነውእንዲያከናውኑ ተወስኗል።

ከቤት ሆነው የሚሰሩ የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችበእያንዳንዱ የሚንስቴር መሥሪያ ቤት አማካኝነት እንደሚለዩ እናማን ከቤት ሆኖ እንደሚሰራ ያስታውቃሉ ተብሏል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው በአዲስ አበባ የሚካሄድ እንቅስቃሴን እናየትራንስፖርት ዘርፉን መጨናነቅ ለመቀነስ ታስቦ ነው።

LEAVE A REPLY