ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ያለውን ግርግር ተገን በማድረግ በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰድን እርምጃ በቅርብ እንደሚከታተሉና በትክክልም እንደሚያስፈጽሙ ገለጹ።
“ጤፍ፣ ሳሙና፣ ውሃና የመሳሰሉት ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የምታደርጉ ነጋዴዎች ድርጊታችሁ ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን ከሰብአዊነት ውጪ ነው” ያሉት ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማ መስተዳደሩ ይህንን ጉዳይ እየተመለከታተለው መሆኑን አስታውሰው፤ “እኔ እራሴ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ከፍ ያለ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በቅርብ እከታተላለሁ። እንደ ሰው በሌሎች ችግር ላይ ማትረፍን አንፈቅድም” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።