ሞዛምቢክ በኮንቴነር ውስጥ ሞተው የተገኙት 64 ኢትዮጵያውያን ተቀበሩ

ሞዛምቢክ በኮንቴነር ውስጥ ሞተው የተገኙት 64 ኢትዮጵያውያን ተቀበሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በስደት ላይ እያሉ ሞዛምቢክ ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኙት 64 ኢትዮጵያዊያን ቀብር ተፈጽሟል።

በኮንቴነር ውስጥ ሞተው የተገኙት እና ለሞታቸው ከመጠን በላይ መተፋፈግና መታፈን እንደሆነ በሞዛምቢክ ባለስልጣናት የተነገረው ኢትዮጵያዊያን የቀብር ስነስርዓት ዛሬ  ሀሙስ ነው ሞዛምቢክ ውስጥ መፈጸሙን የአገሪቱ ባለስልጣናት የገለፁት።

ከአደጋው በህይወት የተረፉት 14ቱ ኢትዮጵያዊያን በሞዛምቢክ የኮሮናቫይረስ ምረመራ ተደርጎላቸዋል::  በውጤቱ ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ቢረጋገጥም ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ሙቀት አላቸው መባሉን ተከትሎ ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስደዋል።

የሞቱት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸው በሚል የተጠረጠሩ  ሁለት ሞዛምቢካውያን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የሞዛምቢክ መንግስት ገልጿል።

LEAVE A REPLY