የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገለጸ

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኮሮናቫይረስ ስጋት ራሳቸውን ለይተው መቀመጣቸው ትናንት ከተነገረ በኋላ ባደረጉት ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ታወቀ።

ዋና ጸሃፊው በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ እንዳሰፈሩት የምርመራ ውጤታቸው ነጻ መሆናቸውን ቢያረጋግጥም በሚታዘዘው መሰረት ለቀጣዮቹ 14 ቀናት እራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩ ገልጸዋል።

በሽታው የተገኘበት ባልደረባቸውን ያለበት ሁኔታን በተመለከተም በመልካመ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ሙሉ ለሙሉ እንዲሻለው ጸሎታቸው እንደሆነ ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊ ሙሳ ፋኪ መጀመሪያ ላይ ጥርጣሬ ያደረባቸው የተጠቀሱት ባልደረባቸው በኮቪድ-19 መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ መሆኑን ተናግረዋል።

በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው የዋና ጸሐፊው ባልደረባ ኢትዮጵያ ውስጥ በሽታው ከተገኘባቸው 16 ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሞሪሼሳዊው የ72 ዓመት ሰው መሆናቸው ተጠቅሷል።

የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጸሃፊው በመልዕክታቸው ላይ በጸሎታቸው ላሰቧቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበው፤ አፍሪካ ከበሽታው ጋር የምታደርገው ፍልሚያ ገና መጀመሩን በማመልከት ሁሉም በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY